የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ የወይን ጠጅ ቀማሾችን (Sommelier Service Provider) አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ/ የጨረታ ቁጥር-SSNT-375
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ብቁ የሆኑ የወይን ጠጅ ቀማሾችን (Sommelier Service Provider) ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- በዘርፉ ለመስራት ለ2015 ዓ.ም. ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
- ለ2015 ዓ.ም የታደሰ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ፍቃድ ያለው፣
- ህጋዊ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ያለዉ
- የወይን ጠጅ የቀማሽነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- በተመሳሳይ የስራ መስክ ቢያንስ የሶስት ዓመት ልምድ ያለው
- ስለ ወይን እና ሻምፓኝ ሰፊ እውቀት ያለው
- የተለያዩ የወይን እና የሻምፓኝ ምርቶች ናሙናዎችን መቅመስ እና አስተያየት መስጠት የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-375 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ሰኞ ሚያዚያ 23 2015 ዓ.ም. ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።
- የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ ወይም የማሻሻል መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517- 49 18
