የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ያገለገሉ ተሽርካሪዎችና እቃዎች ለመሸጥ ይፈልጋል
የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ያገለገሉ ተሽርካሪዎችና እቃዎች ግልፅ ጨረታ
ቢ ዲ አር ኤም ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል/ማህበር
በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ የሚገኘውን የተባሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነርና የዓለም የምግብ መንግስታት የህዝብ ፕሮግራም (WFP) የተባበሩት መንግስታት የህዝብ ፈንድ (UNFPA) የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በመወከል ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችና እቃዎች ለመሸጥ ቅዳሜ ሚያዝያ 21 ቀን 2015 ዓ.ም. 5፡00 ላይ ግልፅ ጨረታ ያካሂዳል።
የተሳታፊዎች ምዝገባ ፣ የተሽከርካሪዎቹ ማየትና የሲፒኦ ማስያዝና ከሀሙስ ሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ/ም እስከ አርብ ሚያዝያ 20 ዓ/ም ዘወትር ከጠዋቱ 3:00 እስከ 10:00 ኮተቤ 02 ቀበሌ ጎል ኢትዮጵያ አጠገብ በሚገኘው መጋዘን ይከናወናል። በጨረታው ቀን መመዝገብ ይሁን ሲፒኦ ማስያዝ አይቻልም
ለመጫረት ፍላጎት ያለው ማንኛውም ግለሰብ ይሁን ድርጅት ብር 500 በመክፈል መመዝገብና ለሚጫረትባቸው ለእያንዳንዱ መኪና የጨረታ መደብ ብር 400,000 (አራት መቶ ሺህ ብር) ለእቃ 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በቢዲ አር ኤም ኃላ/የተ/የግል/ማህበር (BDRM TRADING PLC) ስም እስከ አርብ ሚያዝያ 20 ቀን 2015 ዓ/ም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
አሸናፊዎች ለአሸነፉት ተሽከርካሪ ይሁን ሌሎች የጨረታ መደብ ሙሉውን ክፍያ ጨረታው ከተካሄደበት ቀን አንስቶ ባሉ ቀጣይ አምስት የስራ ቀናት ውስጥ ማለት እስከ አርብ ሚያዝያ 27 2015 ዓ/ም 11፡00 ሰአት ሙሉን ክፊያውን በቢ ዲ አር ኤም ትሬዲንግ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በዳሽን ባንክ አውሮፓ ህብረት ቅርንጫፍ በሚገኘው ሂሳብ ቀጥር 5254001764064 ቀሪውን ገንዘብ መክፈል ይኖርባቸዋል። ከፊል ክፍያዎች ተቀባይነት የላቸውም። በተቀመጠው ጊዜ ገደብ መክፈል ያልቻሉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ያጣሉ ድርጅቱ ሌሎች አማራጮችን የመውሰድ መብቱ የተጠበቅ ነው።
በዚህ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ቀረጥ ያልተከፈለባቸውና “ባሉቡት ሁኔታ እና ቦታ” ለሽያጭ ቀርበዋል። ስለሆነም ከቀረጥ ታክስ ቦሎ እና ስም ዝውውር ጋር በተያያዘ የሚኖሩ ሁሉም ወጪዎች እና ክፍፊያዎች በገዢው የሚሸፈኑ ናቸው። የተሽከርካሪዎች አጠቃላይ ሁኔታ አቋም እና የመስራት ያለመስራታቸው ሁኔታ አውቆ መጫረት ሙሉ ኃላፊነትና ዋስትና በገዥው ውሳኔ ይሆናል። ሻጭ ስለ መኪኖቹ አቋምና ሁኔታ ምንም ኃላፊነት ይሁን ዋስትና አይሰጥም።
ገዢዎች ለገዙዋቸው መኪኖችን አስፈላጊ ሰነዶችን ከተረከቡ በኃላ በ15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊው የግብር የታክስ የቀረጥ ግዴታዎች እና ተያያዥ ወጪዎች ከፍለው በስማቸው አዘዋውሮ መውሰድ ይኖርባቸዋል። አሸናፊዎች የገዙት ተሽከርካሪ መረከብ የሚችሉ በኢትዮጵያ መንግስት ህግና ደንብ መሠረት ለመንግስት መከፈል ያለባቸው የግብር የታክስ የቀረጥ ግዴታዎችና ተያያዥ የስም ማዘዋወሪያ ወጪዎች እና በኢትዮጵያ መንግስት የሚፈለገውን አስፈላጊ ሰነዶችን እና የወረቀት ስራዎችን ካጠናቀቁ በኋላ ብቻ ነው።
አሸናፊዎች የገዙዋቸው ተሽከርካሪዎችና እቃዎች በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ማንሳት ይኖርባቸዋል። በወቅቱ የማያነሱ አሸናፊዎች የማቆያ ክራይና ጥበቃ በቀን 500 ብር ይከፍላሉ።
- ተጫራቾች የገዙዋቸው ተሽከርካሪዎች ሲወስዱ የግል መጓጓዣ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በኢትዮጵያ መንግስት የሚከፈልን ማንኛውም ግብር ቀረጥ የሽያጭ ወይም የስም ዝውውር ክፍያ እና ሌሎች ክፍያዎች የገዢው ኃላፊነት ነው። እነዚህ ወጪዎች ከሽያጭ ዋጋ የማይቀነሱ ይሆናል።
- ሁሉም ተሽከርካሪዎች ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ እንዲሁም በማይመለስ መልኩ ይሸጣሉ።
- ድርጅቱ ከላይ የተቀመጡት መስፈርቶች ሳያሟሉ ወይም ለቀረበው የጨረታ መደብ ተመጣጣኝ ዋጋ አልተሰጠም ብሎ ካመነ ከተጫራቶች የተሰጠው ዋጋ ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ 0945 55 55 50 ወይም 0907 76 77 77 ይደውሉ።
