ገነተ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጃፓን ቶዮታ ፒካፕ ድርብ ተግባር ያለው ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የመኪና የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ገ/ል/ኃ/የ /የ/ማ/ጨ/01/07/2015
- ሎት 1፡ የተሽከርካሪ ሽያጭ
ገነተ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 755 ሕንፃ ውስጥ የሚገኝ ጃፓን ቶዮታ ፒካፕ ድርብ ተግባር ያለው ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው ሁኔታ፣ የጨረታ ሰነዱን ገዝተው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾ ይህ ጨረታ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 755 በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስና አስተዳደር ቢሮ 1ኛ ፎቅ በአካል ተገኝተው የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በመክፈል የመኪናውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።
- ለጨረታ የቀረበውን መኪና የጨረታ ሰነዱን ከገዙ በኋላ የጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ3፡00 ሰዓት እስከ 9፡00 ሰዓት አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 755 በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር ለጨረታው ማስከበርያ ዋስትና የሚውል፣ በገነተ ልማት ኃ.የ.የ.ማህበር ስም ብር 50,000.00 (ሃምሣ ሺህ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- እያንዳንዱ ተጫራች በገዛው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
- ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 755 በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስና አስተዳደር ቢሮ 1ኛ ፎቅ ውስጥ በሚገኝ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ዘወትር ከ3፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው መኪና ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር በተጠቀሰው መኪና ላይ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውንም ወጪዎች ይከፍላል።
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛ የስራ ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 11ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በተገለፀለት በ10 ቀናት ውሰጥ የጨረታውን ዋጋ በመክፈል መኪናዉን መውሰድ አለበት። አሸናፊው በዚህ ሁኔታ የማይፈዕም ከሆነ፣ አሸናፊነቱ ተሰርዞ፣ ለጨረታ ማስከበርያ ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 616 0006 ወይም 0911 40 45 41 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
- አድራሻ፡ - አፍሪካ ጎዳና ቦሌ ጃፓን፣ኢትዮ ሴራሚክ ፊትለፊት የቀድሞ ኖቪስ ሱፐርማርኬት የነበረበት /ፒያኖ ባር ያለበት ገነተ ልማት ህንጻ 1ኛ ፎቅ
ገነተ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
