የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት የተለያዩ የአይሲቲ ዕቃዎች ፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተርና መሰል ዕቃዎች ግዥ ፣ የተለያዩ መፅሀፍት ግዥ እና ልዩ ልዩ አልባሳት (ብርድልብስ) ፣ መጋረጃና መሰል ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-010/2015
የኢትዮጵያ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች ህጋዊ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
ስለሆነም፡
- ሎት 1-የተለያዩ የአይሲቲ ዕቃዎች ዲስክቶፕ ኮምፒውተርና መሰል ዕቃዎች ግዥ
- ሎት-2 የተለያዩ መፅሀፍት ግዥ
- ሎት-3 ልዩ ልዩ አልባሳት/ብርድልብስ፣ መጋረጃና መሰል/ ግዥ
ከላይ የተዘረዘሩት ሎቶችን ለማቅረብ የሚወዳደሩ ህጋዊ የሆኑ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ፤ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና ሌሎች ተፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ከፍት ሆኖ የሚቆየው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ሰነዱ የሚሸጠው በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ ከ2፡00-11፡00 የአንዱን ሎት የማይመለስ 100 ብር አዲስ አበባ በሚገኘው ዋናው ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 206 ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ በመክፈል ደረሰኝ ይዘው 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 408 የአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው በአየር ላይ በዋለ በ15ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- የጨረታ ፖስታውን ፋይናንሺያል እና ቅድመ መገምሚያዎቹን /ቴክኒካል ሰነድ/ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በእያንዳንዱ ሎት 5000.00 (አምስት ሺህ ብር) በCPO ወይም ባንክ ዋስትና ከቴከኒካል/ህጋዊ ሰነዶች |ኦርጂናል ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይሆናል።
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንደአስፈላጊቱ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ስልክ ቁጥር 011 869 4931/011 646 5554
ከሳህሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
