በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ ደንብ ልብስ ፣ የፅዳት ዕቃ ፣ የህትመት ብቃት ያላቸው እና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ/ የግዥው ሠሌዳ ቁጥር 02/2015
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ ለጤና ጣቢያውን በ2015 ዓ.ም በጀት አመት የሚያስፈልጉ
- ሎት 1፣- ደንብ ልብስ
- ሎት 2፣ የፅዳት ዕቃ
- ሎት 3፣ የህትመት ብቃት ያላቸው እና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት፡_
1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
2. ከላይ ለተዘረዘሩት ሎቶች፦
- ሎት 1 የደንብ ልብስ የCPO መጠን ብር 3,000.00
- ሎት 2 የፅዳት ዕቃ የCPO መጠን ብር 1,500.00
- ሎት 3 ህትመት የCPO መጠን ብር 1,500.00
ለእያንዳንዳቸው ሎት ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንh በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በየሎቱ በመክፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ከፍለ ከተማ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 403 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸı ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 403 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 403 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎትı፣ ሎት2 ፣ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
8. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መከፈቻ ላይ ያልተገኘ ጨረታ ተቀባይነት የለውም
9. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
10. የጥቃቅን እና አነስተኛ የድጋፍ ደብዳቤ ለምታመጡ በጥቃቅንና አነስተኛ ፅ/ቤት ኃላፊ መፈረም አለበት።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ : ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ ያኮና ኢንጅነሪንግ ፊት ለፊት በሚገኘው መግቢያ ወደ ውስጥ 200 ሜትር ገባ ይበሉ።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- የመስሪያ ቤቱ ስልክ ቁጥር (011 859 3090/ 011 896 3687)
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ጤና ጣቢያ
