Tender Detail

Tender Details

  • Deadline21 Apr 2023, 4:18 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Building Materials

የኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ የፋብሪካ መለዋወጫዎች ፣ የኮንስትራክሸን ዕቃዎች ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ፣ የአደጋ መከላከያዎችና የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/2015

የኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ የፋብሪካ መለዋወጫዎች፣ የኮንስትራክሸን ዕቃዎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች፣ የአደጋ መከላከያዎችና የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት፣

  1. ደብረዘይት መንገድ ሳሪስ ከሚገኘው የድርጅቱ ሽያጭ ከፍል በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።
  2. የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀን ከጠዋቱ 2፡00 - 6፡oo እና ከሰዓት በኋላ ከ7:00 -10፡00 ሰዓት ብቻ ነው።
  3. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ሁኔታ እስከ ጨረታው መዝጊያ ጊዜ በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡oo-10:30 ድረስ የድርጅቱ መጋዘን በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡oo ሰዓት ድረስ ድርጅቱ ለጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ያቀረቡትን የመወዳደሪያ ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO በማዘጋጀት ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ ተካቶ መቅረብ ይኖርበታል።
  6. ጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት በ15 ኛው ቀን ከቀኑ 8፡oo ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 15ኛ ቀን የዕረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የመንግሥት የሥራ ቀን ይሆናል።
  7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥር፡-  011 442 3659 በመደወል መረዳት ይቻላል።

ኢካፍኮ አከሲዮን ማህበር

Save Tender