Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Apr 2023, 3:07 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የዳቦ ማሽን መለዋወጫ እና የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ማሽኖች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ኮፒ አቅርበው መሆን አለበት።

ተ.ቁ

የጨረታው ዓይነት

የመዝጊያና የመክፈቻ ቀን

ሎት-1

የዳቦ ማሽን መለዋወጫ

ሚያዝያ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል። የጨረታ ማስከበሪያ ብር 350,000.00

ሎት-2

የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ማሽኖች

ሚያዝያ 10 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል። የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00

 

1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም ለተጨማሪ ዕሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ፣ የአቅራቢነት የድረ-ገፅ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የቲን ሰርተፍኬት ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት እና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት የግዥ አዋጅ መሰረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።

3. ከላይ በመግለጫ ለተጠቀሱት የጨረታ ሰነዶች ለእያንዳንዳቸው ፍላጐት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዶችን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 8 በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ። የጨረታው ሰነድ የሚቀርበው በአካል ቢሮ ድረስ በመምጣት ሲሆን ከዚህ በላይ በዝርዝር ከተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውጪ ዘግይቶ ለሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ኃላፊነት የማንወስድ መሆኑን እንገልፃለን።

4. ተጫራቾቶ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ከጨረታ መክፈቻ ቀን አስቀድሞ ባሉት ቀናት ናሙና ማቅረብ አለባቸው።ከተጠቀሰው ቀን በኋላ የሚመጣ ናሙና ተቀባይነት አይኖረውም።

5. መስሪያ ቤታችን እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

6. የተሰማሩበትን ዘርፍ የሚገልፅ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ሳያመጡ የጨረታ ሰነድ መግዛት አይቻልም።

7. አድራሻ ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ (ጦር ሃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት)

ስልክ ቁጥር 011 371 1948

ስልክ ቁጥር 011 372 7314

ፋክስ ቁጥር 011 371 0901

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ግዥ ቡድን

 

 

Save Tender