የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ፈሰሱ ገብሬ እና በፍ/ባለዕዳ ወ/ሮ አየለች መኮንን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 68715 ፣ 86806 በ23/2/2007 ዓ/ም እና በ28/9/2011 ዓ/ም 25/4/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ በቀድሞው ቀበሌ 10/18 የቤ.ቁ 284 የሆነው ቤት ይዞታው በአቶ ወርቁ ወ/ጊዮርጊስ ስም የተመዘገበ ካርታ ያለው የይዞታው ስፋት በሰነድ (በካርታ) 500 ካ/ሜ ይዞታው አገልግሎቱ ለከባድ ኢንዱስትሪ የተፈቀደ መሆኑ በመንገድ ጥናት 14 ካ/ሜ የሚነካው ሲሆን የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 635,764.68(ስድስት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ አራት ብር ከስልሣ ስምንት ሣንቲም ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን ፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ 03:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
