በሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ማዘጋጀ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ለመኖሪያ እና ለንግድ) የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
- የጨረታው ዙር፡- 1ኛ
- የጨረታ ዓይነት፡- መደበኛ
- በሀዲያ ዞን የሆሳዕና ከተማ አስ/ር ማዘጋጀ ቤታዊ አገልግሎት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በሚደነው አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 በፊደል ተራ ከሀ እስከ ሠ በተዘረዘረው መሠረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች (ለመኖሪያ እና ለንግድ) የተዘጋጀ ቦታን በግልጽ ጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል። በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ተከታታይ የሥራ ቀናት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከማዘጋጃ ቤቱ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ዘርፍ ቢሮ ቁጥር 3 እስከ ቀኑ 11፡ 00 ሰዓት ብቻ መግዛት የሚቻል ሆኑን እናስታውቃለን። ለመደበኛ ጨረታ በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው እስከ 9፡00 ሰዓት ብቻ ነው።
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ብቻ ይሆናል።
- የጨረታው ሳጥን የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በወጣበት 10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይሆናል።
- ቦታውን መጎብኘት ለሚፈልግ ተጫራች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሀ-ግብር መሠረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በወጣበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት በሆሳዕና ከተማ አቢዮ ኤርሳሞ ስታዲየም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይሆናል። ኛውና ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል።
- ስለ ጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታው ሰነድ ማግኘት ይቻላል።
- ማዘጋጃ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉበሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ዌብ ሳይት www.hosannaca.gov.et ማግኘት ይቻላል።
ለተጨማሪ መረጃ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውሎ ማግኘት ይቻላል።
046-555-3645 /046-555-2355/ 046-555-2310
የሆሳዕና ከተማ ማዘጋጃ ቤታዊ አገ/ቶች ጽ/ቤት
ሆሳዕና
