Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Apr 2023, 2:46 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት አላቂ እቃዎች ፣ ቋሚ እቃዎች እና ፈርኒቸር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ለ2015 ዓመት የሚከተሉትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1፡- አላቂ እቃዎች
  • ሎት2፡- ቋሚ እቃዎች
  • ሎት3፡- ፈርኒቸር

1. ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት ፣ የግብር ክሊራንስ ፣ በመንግሥት ዕቃና አገልግሎት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የተሰጠ ፈቃድ ሰርተፍኬት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በሀገር ፍቅር ቴአትር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ ከታህሳስ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከሰኞ እስከ አርብ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 -11፡00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ በብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

3. ማንኛውም ተጫራች በየሎቶቹ ለቀረቡት እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ብቻ ናሙናዎችን የምንቀበል መሆኑን እንገልፃለን። በአካል መቅረብ የማይችሉ እቃውን ይገልፃል በምትሉት በፎቶ ፣ በራሪ ወረቀት እቃውን በሚገልፅ መልኩ ማብራሪያ ማቅረብ ይችላሉ።

4. በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና

  • ለሎት 1 እና 3 3050.00 (ሶስት ሺህ ሀምሳ ብር) እንዲሁም
  • ለሎት 2 5,500.00 (አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር) በፖስታ በማሸግ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ያስያዙት የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።

5. ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ፣ ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ ፣ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ ሁሉም የታሸጉ ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽገው መቅረብ አለባቸው።

6. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ያቀርባሉ።

7. በጨረታ ያሸነፉ ተጫራቾች ከመ/ቤታችን ጋር ውል ከተዋዋሉበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ በሲፒኦ የጠቅላላ ዋጋውን 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

8. የጨረታው ሰነድ መሸጥ ከጀመረበት ከሚያዚያ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት አልፎ በሰነድ ማስገቢያው የመጨረሻ ቀን በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ :- ፒያሳ እሳት አደጋ ወረድ ብሎ ሀገር ፍቅር ቴአትር ግቢ ፋይናንስ ቢሮ

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-011 812 6143/011 812 7669/

ማሳሰቢያ:- ጨረታው የሚከፈትበት 11ኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ የሚሆን ከሆነ በመክፈቻው ሰዓት ሰኞ በ4፡30 ሰዓት ይሆናል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ

የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት

Save Tender