Tender Detail

Tender Details

  • Deadline03 May 2023, 4:37 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Disposal Sale

ዘነበ ፍሬው ሆልዲንግስ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ያገለገሉ ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ከድርጅቱ ሽያጭ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ተሽከርካሪዎቹን ጎተራ ከፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ ጎን በሚገኘው ዘነበ ፍሬዉ ሆልዲንግስ ቅጥር ግቢ ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ማግስት ጀምሮ ዘወትር በሥራ ስዓት መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የተሸከርካሪውን መነሻ ዋጋ 5% (በመቶ) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ማግስት ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል።
  5. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን በመለየት የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በድርጅቱ ሽያጭ ቢሮ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት አለባቸው።
  6. ጨረታው በዕለቱ ሚያዚያ 25/2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ተዘግቶ በቀጣይ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ላይ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  7. የጨረታው አሸናፊ በስልክ/በፅሁፍ አሸናፊነቱ በተገለፀለት 5 ቀናት ውስጥ አጠቃላይ ክፍያውን ከፍሎ ተሽከርካሪውን ማንሳት አለበት፡፡ ተሽከርካሪው ከቀነ ገደቡ ውጪ ሳያነሳ ከቆየ ለእያንዳንዱ ቀን ብር 500 የቦታ ኪራይ ይከፍላል። ተሽከርካሪው ሳይነሳ 30 ቀናት ካለፈው ድርጅቱ ተሽከርካሪውን ለማስረከብ በኃላፊነት አይጠየቅም።
  8. አሸናፊው ከታወቀ በኋላ በጨረታው የተካፈሉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ዋስትና ተመላሽ ይደረግላቸዋል። አሸናፊው ደግሞ ከአጠቃላይ ዋጋው ላይ ይታሰብለታል።
  9. በሌላ ተጫራች ላይ ተመስርቶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
  10. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በመ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ስልክ ቁጥር 011 467 0908 – 011 466 5496
  12. ጎተራ ከሞሃ ለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ፔፕሲ ኮላ ፋብሪካ አጠገብ

ዘነበ ፍሬው ሆልዲንግስ

Save Tender