በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በምሻ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በአቡሹራ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የተማሪዎች መፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ለመሥራት በዘርፍ የተደራጁ ማህበራትን ወይም የግል ተቋራጮችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመሥራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ብ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በምሻ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሥር በሚገኘው በአቡሹራ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የተማሪዎች መፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ለመሥራት በዘርፍ የተደራጁ ማህበራትን ወይም የግል ተቋራጮችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመሥራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ተወዳዳሪው ተጫራቾች፤
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
- የቫት ተመዝጋቢነት ሠርተፊኬት ያላቸው
- የንግድ ምዝገባ ሠርተፊኬት ያላቸው
- የመልካም ሥራ አፈጻጸም ሠርተፊኬት ያላቸው፤
- የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያላቸው
- የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ያላቸው ድርጅቶች በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ከግዥ/ፋ/ን/አስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 16 በአካል በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እንዲገዙና ተጫራቾች ለአቡሹራ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የተማሪዎች መፀዳጃ ቤት ግንባታ ሥራ ለመሥራት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000/ አሥር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚጠበቅባቸው እና የጨረታውን መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ሥራ ቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናል እና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 16 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንዲያስገቡና ጨረታው በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ4፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0910 45 46 56/09 16 67 34 83/0912 80 29 92 መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት በሀዲያ ዞን የምሻ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት
