Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Apr 2023, 1:10 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Stationery Materials

የማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2015 በጀት አገልግሎት የሚሰጡ ዕቃዎች የፅህፈት መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2015 በጀት አገልግሎት የሚሰጡ ዕቃዎች የፅህፈት መሳሪያዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና ያሳደሱ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርቲፊኬት አያይዘዉ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የሚያቀርቡ መሆን አለባቸዉ። ከብር 200,000 /ከሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ለሚፈጸሙ ግዥዎች እና ለኤሌከትሮኒhስ ነከ እቃዎች የቫት ተዝጋቢ መሆን አለባቸዉ። የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 20 /ሃያ ብር/ ብቻ በመክፈል ከማ/ጎን/ ከፍ/ፍ/ቤት የግ/ፋ/ ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  2. ጨረታዉ ከመጋቢት 25/2015 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 9/2015 ዓ.ም በአየር ላይ ቆይቶ ሚያዝያ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በታሸገበት ቀን ልክ ከቀኑ 8፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጨረታዉ ማጎ/ዞን/ከ/ፍ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 በግልጽ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም vጋዊ ወኪሎቻቸዉ በቀኑና በሰዓቱ ካልተገኙ ጨረታዉን ከመክፈት አያግድም። ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ የህዝብ በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  3. የዕቃ ዓይነት እና ዝርዝር መግለጫ |ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ሙሉዉን መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሎት ድምር ከሞሉት ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ ከመ/ቤታችን የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 ከገንዘብ ያዥ በመ/ሂı ለማስያዙ የገቢ ደረሰኝ አስቆርጦ ከሚወዳደርበት ሰነድ ጋር የደረሰኙን ፎቶ ኮፒዉን በማሸግ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ዋና ሰነድ በጥንቃቄ ተሞልቶ በታሸገ ፖስታ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸዉ ቦታ እስከ ሚያዝያ 10/2015 ዓ.ም እስከ ከቀኑ 8፡00 ድረስ ሰነዱን በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ የእቃዉን መጓጓዣና እንዲሁም ማናቸዉም የመንግስት ታhስን ያካተተ ሆኖ መቅረብ አለበት።
  7. መስሪያ ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ:: ዉድድሩ በሎት ድምር ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  8. ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ካለዎት ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛዉ ፍርድ ቤት ግዥ/ክፍያና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመቅረብ ወይም በስልከ ቁጥር 058 111 4440 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ቤት

Save Tender