Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Apr 2023, 12:55 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8/1 መሰረት በ2015 በጀት አመት ለ3ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ቤት ብዛት 32 ፣ ለድርጅት ብዛት 9 በድምሩ 41 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል



የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8/1 መሰረት በ2015 በጀት አመት ለ3ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ቤት ብዛት 32 ፣ ለድርጅት ብዛት 9 በድምሩ 41 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡

  1. መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው /ግለሰብ/ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛት ይቻላል።
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት ይችላሉ።
  3. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል።
  4. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልሆነም ተወካዮችም ሆነ ግለሰቦቹ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በነ/መ/ከ/አስተዳደር ቀበሌ 03 ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ይሆናል።
  5. ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል።
  6. ስለጨረታው ዝርዝር መረጀ ከፈለጉ በጽ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 0192 ወይም 058 445 1360 ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
  7. ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሃሳቦችን /ህጎችን/ ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
  8. መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

Save Tender