የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8/1 መሰረት በ2015 በጀት አመት ለ3ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ቤት ብዛት 32 ፣ ለድርጅት ብዛት 9 በድምሩ 41 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል
የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8/1 መሰረት በ2015 በጀት አመት ለ3ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ ቤት ብዛት 32 ፣ ለድርጅት ብዛት 9 በድምሩ 41 ቦታዎችን በጨረታ ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡
- መጫረት የሚፈልጉ ማንኛውም ሰው /ግለሰብ/ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 3 በመምጣት መግዛት ይቻላል።
- የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡30 ብቻ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በቢሮ ቁጥር 3 ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን በ11፡00 ይሆናል።
- ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን በ3፡00 ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ካልሆነም ተወካዮችም ሆነ ግለሰቦቹ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በነ/መ/ከ/አስተዳደር ቀበሌ 03 ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ይሆናል።
- ይህ ማስታወቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆናል።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጀ ከፈለጉ በጽ/ቤቱ የማስታወቂያ ሰሌዳ ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 0192 ወይም 058 445 1360 ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
- ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ሃሳቦችን /ህጎችን/ ከሚሸጠው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
