የደብረ ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ለንግድ 2 ፣ ለመኖሪያ አገልግሎት 7 እና ለሞቴል 2 በድምሩ 1 የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል
የመሬት ሊዝ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታው አይነት :- መደበኛ ጨረታ
በምስ/ጐጃም ዞን በደ/ኤልያስ ወረዳ የሚገኘው የደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በአዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀስ 1 ከፊደል ተራ “ሀ እስከ “ሠ” በተዘረዘረው መሰረት ለንግድ 2 ፣ ለመኖሪያ አገልግሎት 7 እና ለሞቴል 2 በድምሩ 1 የተዘጋጁ ቦታዎችን በግልጽ ጨረታ በሊዝ ማስተላለፍ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታ መወዳደር የሚፈልጉ ማንኛውም 18 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው ኢትዮጵያዊ የሆነ ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት በመምጣት የቦታውን ዝርዝር መረጃ እና የጨረታዉን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፍል በደ/ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 4 የገቢ አሰባሰብ እና ክትትል ዋና የስራ ሂደት መግዛት ይቻላል።
ስለዚህ፡
- የጨረታ ዙር የ2015 በጀት አመት ሁለተኛ ዙር ጨረታ ነው።
- ቦታውን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ በሚገለጸው መርሃ ግብር መሰረት የምናስጎበኝ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ) የተጫረቱበትን ቦታ ስፋት በቦታው የመነሻ ዋጋ በማባዛት የሚገኘውን ውጤት 5 በመቶ እና ከዚያ በላይ በዝግ አካውንት ቁጥር በማስገባት በባንከ የተመሰከረለት ሰነድ ከዋጋ እና የሃሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በሚዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ሰነዱን ሞልተው ጨረታው በጋዜጣ በወጣ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከ2፡30 እስከ ቀኑ 11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ስለሆነም ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ ከ11፡00 ላይ የሚዘጋ ይሆናል።
- በመጀመሪያ ዙር እና በሁለተኛው ዙር ለአንድ ቦታ ከሶስት ተጫራች በታች ከቀረበ ጨረታው አይከፈትም።
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸው ፊርማቸውን የስልክ ቁጥራቸውን እና አድራሻቸውን በሁሉም ገጽ ላይ ማኖር ይጠበቅባቸዋል። በጨረታው የሚሳተፈው አካል ድርጅት ከሆነ የድርጅቱ ማህተም በሰነዶቹ ሁሉም ገጽ ላይ ማኖር ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው የጨረታ ሳጥን በተዘጋ ቀጣይ የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይሆናል።
- በዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ የሚጫረቱበትን የቦታ ዋጋ በፊደል እና በአሃዝ መሙላት ይኖርበታል። በፊደል እና በአሃዝ በተጻፈው ካከል ልዩነት ካለ በፊደል የተጻፈው ተቀባይነት ይኖረዋል።
- በዋጋና ሐሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ እንዲሁም በግልጽ የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ቦታ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ በቀረበው የቦታ ዝርዝር መረጃ ላይ /በጨረታ ሰነዱ) የተገለጸውን ለመክፈል በዋጋ መሙያና ሐሳብ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
- ለጨረታ ለቀረቡ ቦታዎች ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ እና ሌሎች የሚገቧቸውን ግዴታዎች ሞልተው የሚቀርቡበት ለጨረታው በተዘጋጀው የጨረታ ማቅረቢያ ኦርጅናል ቅጽ አማካኝነት ብቻ ነው።
- ከላይ የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ የጨረታ ሰነድ ማቅረቢያ ጊዜ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ በጽ/ቤቱ በኩል ካጋጠመ ለተጨማሪ 7 የስራ ቀናት የሚቆይ ሰነድ ሽያጭ ማቅረቢያ ጊዜ እና ጨረታው የሚከፈትበትን ተለዋዋጭ የስራ ቀን እና ሰዓት በልዩ ልዩ መንገድ የሚያሳውቅ ይሆናል።
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጀ ከተቋሙ ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ 058 250 0230 ወይም 058 250 0668 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የደብረ ኤልያስ ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት
