ሀገረሰብ ሪል እስቴት አ.ማ. ከ2014-2016 በጀት አመት ለ3 አመት የሚቆይ የሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) ስራ በተፈቀደለት እና በተመሰከረለት የውጪ ኦዲተር የሂሳብ መዝገብ ለማስፈተሽ እና ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ይፈልጋል
የሒሳብ ምርመራ (ኦዲት ሥራ) ጨረታ ማስታወቂያ
ሀገረሰብ ሪል እስቴት አ.ማ ከ2014-2016 በጀት አመት ለ3 አመት የሚቆይ የሂሳብ ምርመራ (ኦዲት) ስራ በተፈቀደለት እና በተመሰከረለት የውጪ ኦዲተር የሂሳብ መዝገብ ለማስፈተሽ እና ለማስመርመር (ኦዲት ለማስደረግ) ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ኦዲተሮች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
ተወዳዳሪዎች ሊያሟሉት የሚገባ መስፈርት
- በኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝ እና ኦዲቲንግ ቦርድ ወይም እሱ በሚወክለው አካል ሂሳብ ለመመርመር የሚያስችለው የሙያ ፍቃድ ማረጋገጫ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችል ፤ የ2014 በጀት አመት ግብር ስለመክፈሉ የግብር ክፍያ ምስክር ወረቀት (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችል፤
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
- ተወካዩ ሂሳብ መርማሪ ወይም ከሂሳብ መርማሪ ቡድን አባላት ውስጥ ቢያንስ አንዱ ከዚህ በፊት የሪል እስቴት ድርጅቶችን ሂሳብ የመረመረ መሆን አለበት
- ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎቱ የሚያስከፍሉትን ዋጋ ፣ የሂሳብ ምርመራ ስራውን ሰርተው አጠናቀው ዘገባውን (Report) የሚያስገቡበትን ጊዜ የሚገልፅ መዘርዝር (Proposal) ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች የ2014 በጀት አመት የሰነድ ብዛት 3 ቦክስ-ፋይል እስከ የካቲት 30, 2015 ድረስ የ2015 በጀት አመት የሰነድ ብዛት 5 ቦክስ-ፋይል ደርሷል እስከ ሰኔ 30, 2015 ድረስ እየጨመረ ሊሔድ እንደሚችል መገንዘብ አለባቸው።
ተወዳዳሪዎች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከታች በተጠቀሰው አድራሻ መሠረት ሰነዶቹን በታሸገ ኤንቨሎፕ ዘወትር በስራ ሰዓት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ሪል እስቴቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ:- ሪቼ አልፋ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ
ስልክ:- 0912 65 67 58 | 0930 60 11 61
ሀገረሰብ ሪል እስቴት አ.ማ.
