Tender Detail

Tender Details

  • Deadline15 Apr 2023, 11:25 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 003/2015

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ

  • ሎት 1.  የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 2. አላቂ የጽህፈት እቃ፣
  • ሎት 3. አላቂ የጽዳት እቃ፣
  • ሎት 4. የህክምና መድሃኒቶችና መገልገያ መሳሪያዎች፣
  • ሎት 5. ቋሚ እቃ፣
  • ሎት 6. የህትመት ሥራ ውጤቶች፣
  • ሎት 7. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃና የጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች፣
  • ሎት 8. የቴራዞ ስራ፣
  • ሎት 9. የሽንት ቤት ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎትና ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾቾ ማሟላት የሚገባችሁ መስፈርቶች:-

1. በተሰማራችሁበት የስራ መስክ የንግድ ፍቃድ፤ የአቅራቢነት ማስረጃና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የሚቀርብ ማስረጃ

2. በመንግስተ የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ።

3 ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተመላሽ የሚሆን የጨረታ ማሰከበሪያ ቢድ ቦንድ ሲፒኦ

  • ሎት1. ለደንብ ልብስ፣ 5,000 (አምስት ሺህ ብር)
  • ሎት2. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች 2000 (ሁለት ሺህ ብር) ፤
  • ሎት3. አላቂ የጽዳት እቃዎች 1,500 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር)፤
  • ሎት4. የህክምና መድሃኒቶች እና መገልገያ መሳሪያዎች ፤ 6000 (ስድስት ሺህ ብር)
  • ሎት5. ቋሚ እቃ 4000 (አራት ሺህ ብር)
  • ሎት6. የህትመት ሥራ ውጤቶች 2000 (ሁለት ሺህ)፤
  • ሎት7. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃና የጥገና መለዋወጫ ዕቃዎች 5000.00 (አምስት ሺህ ብር ብቻ)
  • ሎት8. የግቢ የቴራዞ ስራ 6000 (ስድስት ሺህ መቶ)
  • ሎት9. የሽንት ቤት ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት 1000 (አንድ ሺህ ብር) እንዲሁም ተጫራቾች 2 እና ከ2 በላይ የጨረታ ሰነድ (ሎት) የሚገዙ ከሆነ ብር 8,000(ስምንት ሽህ ብር) በባንከ በተመሰከረ ሲፒኦ /CPO/ በፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ ስም ከጨረታ ሠነዱ ጋር አብሮ ማስገባት አለባቸው።

5. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) (መክፈል ከቢሮ ቁጥር 415 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።

6. የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለአስር ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ይውላል።

8. ተጫራቾች የዶክመንታቸውን ዋናውንና ፎቶኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ በተነገራቸው በ15 ቀን ውስጥ ቀርበው ውላቸውን በመፈፀም የውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ በባንከ የተረጋገጠ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

10. ተጫራቾች በሚያቀርቡበት ዋጋ ላይ ቫትን ጨምረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ካልተጠቀሰ እንደተጠቀሰ ተደርጎ ይወሰዳል።

11. የጨረታው ሳጥን የሚዘጋው ጨረታው በወጣ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ይዘጋል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በስራ ቀን በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።

12. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈረመበት ጀምሮ በ15 ቀን ውስጥ እቃውን ያቀርባል ጥገናውን እና አገልግሎቱን ይሰጣል፡፡

13. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ ወይም ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል ይችሉም

14. ተጫራቾች የዋጋ ዝርዝራቸውን በዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ሞልተው እና በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ማንኛውም የጥቃቅን ተጫራች ከአደራጃቸው አካል አምራች ሆናቸውን የሚገልፅ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ፡- አ/ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ ከፓስተር ወረድ ብሎ ወደ ወረዳ 06 መሄጃ መንገድ ላይ ይገኛል።

ስልክ ቁጥር፦ 011 895 9478

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ፅ/ቤት የፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ

Save Tender