ብርሀን በር ቅድመ መጀመሪያ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ አላቂ የህክምና ዕቃዎች ፣ አላቂ የትምህርት ዕቃዎች እንዲሁም ቋሚ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 3/2015
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አአክ ብርሀን በር ቅድመ መጀመሪያ እና የመጀመሪያ ደረጃ ትቤት ከመንግስት ከተደበለት መደበኛ የውስጥ ግቢ በጀት እና ከድጎማ በጀት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ አይነት ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚም መሰረት፤
- ሎት 1 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- ሎት 2 አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣
- ሎት 3 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች፣
- ሎት 4 ቋሚ ዕቃዎች ለመግዛት የሚፈልግ ስለሆነ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
ተጫራቾች የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፣ ወቅታዊ የግብር ግዴታቸውን የተወጡና በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ እንዲሁም በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ሊስት ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል። ተራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከብርሀን በር ቅድመ መጀመሪያና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ክፍል ከጠዋት 2፡30–11፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሰነዱን አሽገው ዋናውን እና ኮፒውን ለያይተው ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በ11ኛው በሥራ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የተጫረቱበትን ዕቃዎች ናሙና Iሳምፕል/ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ውል ከመፈረማቸው በፊት የውል ማስከበሪያ የተጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ ቫትን ጨምረው ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው መሙላት አለባቸው።
- ብርሀን በር የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በጨረታው ከሚቀርቡት የዕቃዎች ብዛት አሸናፊ ከሆነው ድርጅት እስከ 20% ድረስ ለመቀነስ ወይም ለጨመር መብት አለው።
- ማንኛውም ተጫራች ለናሙና |ለሳምፕል ያስያዘውን ዕቃ የጨረታ ውጤት ከተነገረ በኋላ በ10 ቀናት ውስጥ መውሰድ አለበት ከዚህ ቀን ውጭ ዘግይቶ ለሚመጣ ተጫራች በቂ ማስቀመጫ ቦታ ስለሌለ ቢበላሽ፤ አይጥ ቢበላው ሃላፊነቱን የማንወስድ መሆኑን እናስታውቃለን።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሎት 1 እስከ ሎት 4 ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 1000.00
አንድ ሺ ብር በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማስገባት
ይኖርባቸዋል። - ተጫራች የጨረታ ማስያዣ ሲፒኦ ዋናው ሰነድ ውስጥ ማስገባት አለበት።
- ከተቋሙ የገዛችሁትን የጨረታ ሰነድ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታችሁን ማህተም ማድረግ ይኖርባችኋል። ጥቃቅን እና አነስተኛ የሆናችሁ ከምታመርቱት ውጪ የምትወዳደሩ ከሆነ ሲፒኦ እና ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ/መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ፡- አጠና ተራ ወረዳ 10 ከተቃጠለው ህንፃ ፊት ለፊት ስልክ ቁጥር 011 279 2458 /011 273 9672 ማሳሰቢያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአ/ከ/ክ/ከ የብርሃን በር ቅድመ መጀመሪያ እና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
