በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት የእንስሳት ጤና ኬላ እና የህክምናና የክትባት በረት ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ/ብ/ህ/ክ/መ በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ከወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በ2015 በጀት ዓመት በአውሮፓ ህብረት በተላከው በጀት በደንዶ ወርቅቻ ና ፋንጎ ሁምቦ ቀበሌ ለሚያስራው የእንስሳት ጤና ኬላ እና የህክምናና የክትባት በረት ግንባታ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት መጫረት የምትችሉ ተጫራቾች፡ -
- የ2015ዓ.ም. ፈቃዳቸውን ያሳደሱ ፤የታደስ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ቲ.ኢትቫት /ተመዝጋቢ የሆኑ፤ቲን መለያ ቁጥር ያላቸው፤ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውና / በፌዴራል ግዥና የመንግስት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ምዝገባ/በበይነ መረብ የተመዘገበ ማቅረብ የሚችሉ እና GC/BC ደረጃ 6 እና ከዛ በላይ ያላቸው።
- ተጫራቾች 2% ለመንግስት ግብር እንደሚቆረጥ ማወቅ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 400.00(አራት መቶ) ብር በመከፈል ከወ/ዞድ/ፋ⁄ወ/ፋ⁄ኢ/ል/ጽ/ቤት የንግድ ፍቃዳቸውን ዋናውን በመያዝ ከቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸውን ቴhኒካል ግምገማ መስፈርቱን ከዋናው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤ (የጨረታው ሰነድ ከጨረታ ማስታወቂያ ጋር እኩል ዋጋ ይኖረዋል)፤
- ተጫራቾች በአሁኑ ሰዓት ያላጠናቀቁና በውል ያላስረከቡ ፕሮጀhት በእጃቸው ካለ ጨረታውን መወዳደር ብቁ አይደሉም ወይም ከጨረታው ውጪ ይሆናሉ (ተጫራቾች ፕሮጀክቱን ያጠናቀቁበትን የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ ይኖርባቸዋል)፤
- በማንኛውም ቦታ ለግንባታ ሂዲት /በማንኛውም ሥራ ዘርፍ /ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው ላለፋት ቅርብ ዓመታት፣
- ጨረታው ተቀባይነት የሚኖረው ከተከፈተበት እስከ 60 ቀናት ብቻ ነው።
- እያንዳንዱ ዶክመንት በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልተው ቴክኒካል እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ሁሉንም ለየብቻቸው ታሽገው እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው በማቅረብ ሁሉም ዶክመንት በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በሰም አሽገው ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/cpo/ ካሽ ብር 38,000 (ሰላሳ ስምንት ሺህ ) ጨረታው ከተከፈተ ለ60 ቀናት የሚቆይ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ባንክ ጋራንት እና ኢንሹራንስ ቦንድ ማቅረብ አይቻልም።
- ተጫራቾች የመስክ ምልከታ ድጋፍ ከወረዳው ግብርና ልማት ጽ/ቤት መቀበል ይኖርባቸዋል፤(ሳይት ምልከታ ያልያዘ ተጫራች ለመወዳደር ብቁ አይደሉም ወይም ከጨረታው ውልቅ ይሆናሉ)።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለባቸውም።
- ስለዚህ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በ21/ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 2፡30pm ከሰዓት ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን የሚቆይ ሲሆን 21ኛው ቀን በዓል እና ሰምበት ከሆነ ቀጣይ በሥራ ቀን 2፡30 PM ከላይ የተገለፀውን መሥፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመግለጽ ፖስታውን በሰም አሽገው ዘወትር በሥራ ሰዓት ድ|ፋ|ወ/ፋ|ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስተዳደር ዋና የሥራ ሃደት ጨረታ ከፊል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማኖር ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ባልተገኙበትም ልክ ከቀኑ 3፡00 PM ሲሆን የፖስታ ሳጥን በ2:30PM ከሰዓት ታሽጎ 03:00PM ከሰዓት ይከፈታል።
- 9 በሂሳብ ስህተት ማስተካከያ የሚመጣውው የተጫራቹ ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መከፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ከተነበበው ጠቅላላ ዋጋ ከ2% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ሆን የለበትም።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ማሳሰቢያ፡- የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር /0919 65 74 41/0916 71 99 03/0919 98 07 60
በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ቢጠና
