በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ማእከላዊ ጎንደር ላይ ያለውን መጋዝን አጥር ደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን በማወዳደር ማሳጠር ፣ የመኪና ጎማ እና ላፕቶፕ ኮምፒውተር ለመግዛት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ማእከላዊ ጎንደር ላይ ያለውን መጋዝን አጥር ደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾችን በማወዳደር ማሳጠር፣ የመኪና ጎማ እና ላፕቶፕ ኮምፒውተር ለመግዛት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራትና መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢነት ሰርቲፊኬት እንዲሁም ቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው ሆኑን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ። ለግንባታ ስራው የምዝገባ ወረቀት ፣ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንዲሁም ደረጃ 8 እና ከዚያ በላይ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 እስከ 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- የእቃው /የስራው/ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሪ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኘ ገቢ በማድረግ ወይም ከቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ ተቋማት የመልካም ስራ አፈጻጸም ዋስትና የሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለጎማው እና ላፕቶፕ ኮምፒተር እስከ 5 ተከታታይ ቀን ድረስ ለግንባታው አስከ 21 ተከታታይ ቀን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ /መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ግንባታው 21 ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ22ተኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ጎማ እና ላፕቶፕ ኮምፒተር አስከ 15 ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምከንያት ባይገኙ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው።
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ ይቻልም።
- የገዥ መ/ቤት አድራሻ አ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ባህር ዳር
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 058 218 0014/ 058 281 1103 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአብክመ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን
