የሲ/ብ/ክ/መ ለሸበዲኖ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሳዴቃ ፣ ፉራ ፣ዲላ-ጉምቤ እና ዲላ-አፋራራ መንገድ ላይ ዶዘር ለማስገባት የከፍታ ስራ ፣ ቆርጦ የመሙላት ስራ ፣ ጉቶ የመንቀል ስራ እንዲሁም አስፈላጊ ስራዎችን ለማሰራት ብቁ የሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የሲ/ብ/ክ/መ ለሸበዲኖ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሳዴቃ ፤ ፉራ ፤ ዲላ-ጉምቤ እና ዲላ-አፋራራ መንገድ ላይ ዶዘር ለማስገባት የከፍታ ስራ ፤ ቆርጦ የመሙላት ስራ ፤ጉቶ የመንቀል ስራ እንዲሁም አስፈላጊ ስራዎችን ለማሰራት ብቁ የሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት መጫረት የሚችሉ ፡
- የማሽነሪ ኪራይ ፈቃድ ያላቸውና ፈቃዳቸውን ያሳደሱ እና ደረጃ (5) አምስት ያላቸው
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- በስራ ሂደቱ ማንኛውም ማስጠንቀቂያ ያልተሰጣቸው
- የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 20000(ሃያ ሺህ) የሚሆን ብር በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ
- ከዚህ በፊት የመንገድ ስራ የሰራበት የስራ ልምድ payment certificate and good performance ማቅረብ የሚችል
- Time schedule ማቅረብ የሚችሉ
- ቴክኒካል ኦሪጅናልና እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ
- ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ
- የማይመለስ ብር መቶ ብር በመክፈል የስራ አይነት የሚገልጽ ሰነድ ከገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ
- ስለዚህ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ ለ15(አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ የእያንዳንዱን ዋጋ በመግለጽ በፖስታ አሽገው ዘወትር በስራ ሰዓት ሸ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ክ/ን/አስ/የስራ ሂደት ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማኖር ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኑበት በ16ኛው ቀን ሲሆን ቀኑ እሁድና ቅዳሜ ከሆነ ቀጣይ የስራ ቀናት በፖስታ ሳጥኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል። እለቱ የበአል ቀን ወይንም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በተመሳሳይ እለት በቀጣይ ቀን ይከፈታል።
- ጽህፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም
ስልክ ፡- 046 226 0284/0916 15 61 17
የሲ/ብ/ክ/መ/ በሸበዲኖ ወረዳ ፋይናንስ/ኢኮ/ልማት ጽ/ቤት
