የሻሁራ ከተማ አስተዳር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2015 በጀት አመት ለመንግድ ግንባታ ስራ የሚያገለግሉ የማሽን ኪራይ (ግሬደር ፣ ኤክስካቫተር ፣ ሻወር ትራክ ፣ ሮሎ ፣ ገልባጭ) በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሻሁራ ከተማ አስተዳር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2015 በጀት አመት ለመንገድ ስራ አገልግሎት የሚዉል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ማሽነሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል።
ሎት.1 ለመንግድ ግንባታ ስራ የሚያገለግሉ የማሽን ኪራይ (ግሬደር፣ ኤክስካቫተር ፣ ሻወር ትራክ ፣ ሮሎ ፣ ገልባጭ) በግልፅ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለዚህ በጨረታዉ ለመሳተፍ የምትፈልጉ አቅራቢዎች ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግዴታወች ማሟላት ይኖርባችኋል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብር ከፋዩች መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
- የኪራዩ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚህ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ ስለመሆናቸዉ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ከማጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ የሚችሉ።
- የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ዉድድሩ በጥቅል ወይም በሎት ስለሆነ ሁሉም መሞላት ይኖርባቸዋል።
- የሚከራዩ ማሽኖች በተጠየቀዉ ዝርዝር መግለጫ መሰረት ሆኖም የጨረታ ሰነድን ሻ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-1 የማይመለስ ብር 100 ብር በመክፈል ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ወይም የኪራዩን ጠቅላላ ዋጋ 1.5 በመቶ በባንክ ከተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ። በጥሬ ገንዘብ የሚያስይዙ ተጫራቾች የገቢ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በማስቆረጥና ደረሰኙን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስምና አድራሻ በመፃፍ ፊርማና ማህተም በማድረግ ከሻ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር- 1 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስታወቂያዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በግዛት ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 25/7/15 ዓ.ም. ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አየር ላይ ይዉላል። በ16ኛዉ ቀን ማለትም በ እስከ በ10/08/15 ዓ.ም. እስከ ጠዋቱ 3፡00 ድረስ የመጫረቻ ሰነዳቸዉን ከተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ። ጨረታዉ በ16ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በሻሁራ ከተማ አስ/ገ/ኢ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል ላይ ማህተም ማድረግ አለባቸዉ።
- መ/ቤቱ ጨረታውን 20 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የኪራዩን ዋጋ የሚሞላው ከጨረታው ጋር በምናቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ሆኖ ስፔስፊኬሽን ቀይሮ መሙላት የተከለከለ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በዚያው ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ ለመጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 270 0526/ በአካል በመምጣት መጠየቅ ይችላሉ።
- የሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
የሻሁራ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
