የግዮን ሆቴሎች ድርጅት የተለያዩ አልባሳት አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዮን ሆቴሎች ድርጅት
- የሠራተኞች የደንብ ልብስ ጨርቆች አቅርቦት (ከነእጅ ሥራው)
- ከደንብ ልብስ ጋር የሚለበሱ የወንድና ሴት ሸሚዞች
- ከደንብ ልብስ ጋር የሚለበሱ ወንድና የሴት ጫማዎችን አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም
ከላይ የተገለፁትን ዕቃዎች ማቅረብ አንችላለን የሚሉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል::
- የ2015 የታደሰ የንግድ ፍቃድ ሰርተፍኬት ያለው
- የታደሰ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያለው
- Tin No /የግብር መለያ ቁጥር/ ሰርተፍኬት ያለው
- Vat/ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያለው
- የተጠቀሱትን ዕቃዎች በማቅረብ ልምድ ያላቸው
- በሚወዳደሩባቸው የጨረታ ዘርፎች ለሚያቀርቡት ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ
- የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታው ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለደንብ ልብስና ጫማ ለእያንዳንዱ የጨረታ አይተም ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለሸሚዝ በመክፈል የጨረታው ሰነድ ከድርጅታችን ግዥ አገልግሎት ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ በወጣበት በ21ው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ዕለት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 551 3222 Ext. 5429/5163 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የሥራ ሰዓት፡ ከሰኞ እስከ ሀሙስ ጠዋት 2፡00 - 6፡00 ከሰዓት 7፡00 - 11፡00
አርብ ጠዋት ከ2:00 - 5:30 ከሰዓት 7:30 እስከ 11:00
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ግዮን ሆቴሎች ድርጅት
