ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና አሁን በሚገኙበት ይዞታ ላይ እንዳሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር፡015/22/23
ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታና አሁን በሚገኙበት ይዞታ ላይ እንዳሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ መነሻ ዋጋውን 1/4(አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲ.ፒ.ኦ. በደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው ለመሳተፍ ይችላሉ።
- የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ ከባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ በጨረታ ያሽነፈበትን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ. ይመለስላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ፣ ከግብር ጋር በተያያዘ የሚከፈል ካለ ፣ በሽያጩ ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጪዎች ይከፍላል።
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ሁኔታ ስታዲየም አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ናሽናል ታወር ምድር ቤት (parking) ባንኩ በሚያዘጋጀው የጉብኝት መርሀ ግብር መሰረት በአካል ቀርበው መመልከት/መጎብኝት/ ይችላሉ ፣ አንድ ተጫራች አንድ መኪና ላይ ብቻ መጫረት ይችላል።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሽከርካሪ የሚያቀርቡትን የመግዣ ዋጋ ፣ የሰሌዳ ቁጥር እና ኮዱ እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ በግልጽ (ስርዝ ድልዝ የሌለው) በማስፈርና ከጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ጋር አያይዘው በማሸግ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የተሸከርካሪዎቹን ሞተር እና ሌሎች አካላት ፍተሻ ማድረግ አይችሉም።
- በአንድ ተሽከርካሪ ከሁለት በላይ ተጫራቾች እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ አሸናፊው በእጣ ይለያል።
- ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በባንኩ ዋናው መ/ቤት ናሽናል ታውር ሕንጻ 11ኛ ፎቅ (ስታዲየም ከኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ) በሚገኘው እስከ ሚያዚያ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዚያ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው እለት ጠዋት 4፡30 በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ለበለጠ ማብራሪያ ደቡብ ግሎባል ባንክ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት በስልክ ቁጥር 011 558 1204/011 531 8156 ደውሎ መረዳት ይቻላል።
- ባንኩ ንብረቶቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
|
ተ.ቁ |
የተሽከርካሪው ዓይነት |
ሞዴል |
ታርጋ ቁጥር
|
ቻንሲ ቁጥር
|
ሞተር ቁጥር
|
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
|
1 |
Nissan Micra Automobile 2012 |
FDWULCG K134G5**A*
|
3-82427 አ.አ
|
MDHFBUK 13Z0010929
|
HR1275 8032A
|
850,000.00
|
|
2 |
Bishoftu Double Cabin Pick up 2012 |
DD1022T
|
3-98678 አ.አ
|
EBPH4C4BB 463000698
|
4JB1TI*210 20424A*
|
750,000.00
|
|
3 |
Suzuki Motor Bicycle 2012 |
TS185
|
3-1796 አ.አ
|
ISISG12 A352113222
|
TS1852-189660
|
65,000.00
|
|
4 |
TVS Motor Bicycle 2013 |
TVS
|
3-2032 አ.አ
|
MD625DF 46D1G15255
|
AF4GD 1064523
|
45,000.00
|
|
5 |
Hyundai EON Automobile 2015 |
EON |
3-A30384 አ.አ
|
MALA251A AGM439664
|
G3HAFM 400005
|
750,000.00
|
