ዮንአብ ኮንስትራክሽን ለጋቢዮን ኮንስትራክሽን ስራ የሚውለውን የጋቢዮን ሽቦ እና ጂኦሜምብሬን ልዩ እቃ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
YONAB CONSTRUCTION
የጋቢዮን ሽቦ እና ጂኦሜምብሬን ግዢ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር- አዳማ/01/15
ድርጅታችን ዮንአብ ኮንስትራክሽን ለጋቢዮን ኮንስትራክሽን ስራ የሚውለውን የጋቢዮን ሽቦ እና ጂኦሜምብሬን ከዚህ በታች በተጠቀሰው ሰንጠረዥ ልዩ የእቃ ዝርዝር መስረት የአቅርቦት ፍላጎት ካላቸው ድርጅቶች ላይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
Item no |
Description |
unit |
Qty
|
|
1 |
Gabion box with wire internal diameter 2.5 mm zink coated (galvanized), box size 2m*1m*1m and mesh size 80mm x 100mm mesh |
No
|
1,248 |
|
2 |
Geo- Textile filter fabric |
m2 |
1,931 |
ስለሆነም በጨረታ መካፈል የሚፈልጉ ማንኛውም አቅራቢ ድርጅቶች፡
- የታደሰ የዘመኑ ንግድ ሥራ ፍቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው እና ቫት ለመዝጋቢ መሆን ይገባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው እቃዎች በቅድመያ ናሙና አቅርበው የእቃው ጥራት የ3ኛ ወገን የጥራት ማረጋገጫ ማግኘት አለበት።
- ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) ብር በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከዋናው መስሪያ ቤት ኡራኤል ወደ አትላስ በሚወስደው መንገድ ላይ 300 ሜትር ገባ ብሎ አዋሽ ኢንሹራንስ ህንፃ ላይ ከሚገኘው ዮንአብ ኮንስትራክሽን ሶስተኛ ፎቅ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በድርጅታችን ሥም የተዘጋጀ የብር 100,000.00(አንድ መቶ ሺህ) ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሰነዶች ጋር በታሸገና የተጫራች ድርጅት ማህተም ያረፈበት ፖስታ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት ተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ከ ቀኑ 8፡00 ሰአት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ።
- ጨረታውም በተመሳሳይ ቀን ከ ቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
