የአለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2015 የበጀት ዓመት የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ የመኪና እና የሞተር ጎማዎች ፣ የደንብ ልብስ እና ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳድር በሰሜን ሸዋ ዞን የአለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2015 የበጀት ዓመት
- የተለያዩ ቋሚና አላቂ እቃዎች ፣
- የጽዳት እቃዎች ፣
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣
- የመኪና እና የሞተር ጎማዎች ፣
- የደንብ ልብስ እና
- ፈርኒቸሮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
የጨረታ መመሪያ፡
- እቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ ለዚህም ከሚመለከተው አካል ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል።
- በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጭ አካላት በአቅራቢዎች ዝርዝር ዉስጥ የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ብቻ በጨረታዉ ይካፈላሉ፡፡
- በግልም ሆነ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ዋጋችሁን ስታቀርቡ የአንዱ ዋጋ ሆነ የጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ (VAT) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስም /brand name/ እና የእቃዉ ጥራትና ደረጃ /መለያው/ መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሠነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም፡፡
- መሥሪያ ቤታችን የሚያጫረታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፍኬሽን መሠረት ተሟልተው ካልቀረቡና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈጽም ኃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው።
- ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ ዓይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ በነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የጠቅላላ ዋጋ ይወሰዳል፡፡
- ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
- ለጨረታው የሚቀርበው ሠነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መፃፍ አለበት፡፡
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት በፍጹም አይቻልም፡፡
- ለጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (ለአስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300/ ሦስት መቶ ብር / በመክፈል አለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቀርበው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ከ15/አስራ አምስት/ የሥራ ቀን ቆይቶ በ3/1/2015 ዓ.ም. ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት ከቀኑ 8፡00 /ስምንት ሰአት/ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የምታቀርቡትን ዕቃዎች አይነት /ናሙና/ ዘወትር በሥራ ሰዓት በመ/ቤታችን ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በማምጣት አለባቸው፡፡ ናሙናውን ከወጣው ዝርዝር መግለጫ ወይም እስፔሲፊኬሽን ጋር ማስተያየት ያስፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ለምን ዓይነት ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቸው ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ከዚህ በላይ በተገለፀው መመሪያ መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈፅሙ ቢቀሩ ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘ ገንዘብ ለጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
አድራሻ :-በደሴ መንገድ በዋናው አስፋልት ከአ/አ 55 ኪ.ሜ በስተቀኝ 150 ሜትር ገባ ብሎ ነው።
በስልክ ቁጥር 0116310305/0209 የአለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጠየቅ ይችላሉ።
የአለልቱ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
