የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2015 አ.ም. የውድድር ዘመን ለተጫዋቾች የምግብ አገልግሎት ፣ የስፖርት ቁሳቁሶችን እና የከባድ መኪና ጎማ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመገልገልና ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ በ2015 አ.ም. የውድድር ዘመን ለተጫዋቾች
- የምግብ አገልግሎት፣
- የስፖርት ቁሳቁሶችን እና
- የከባድ መኪና ጎማ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመገልገልና ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ማሟላት የምትችሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ እየጋበዝን
- በየዘርፉ የተሰማራችሁ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው የቫት ተመዝጋቢ የሆነ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰና የዘመኑን ግብር የከፈለ ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ጨረታ 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል።
- አሸናፊ ድርጅት ለመልካም የሥራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት/ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና የውሉን የጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ ማስያዝ የሚችል
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ በአ/ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን እንዲገዙ እየገለጽን እያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ መግለጫውን በማያሻማ መልኩ እና ስርዝ ድልዝ ሳይኖር በመሙላት ሁሉም የጨረታ ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ በድምሩ 2 ፖስታዎች በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከፊትና ጀርባው ላይ የድርጅቱን ማህተምና የባለቤትነት ፊርማ በማድረግ በእናት ፖስታ ውስጥ ተጨምሮ ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ቅዳሜና እሁድን ያካተተ ይሆናል
- በጨረታው ያሸነፈ ተወዳዳሪ የባለሙያ አስተያየት ላይ መሠረት በማድረግ ውል ገብተው ወደ ስራ የሚገባ ይሆናል።ሁሉም ተጫራች አድራሻቸውንና ቦታውን እንዲሁም የስልክ ቁጥር መግለጽ ይኖርበታል። በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
- የእያንዳንዱ ግዥ መጠን በሽያጭ ሠነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ሃያ በመቶ ሊጨምርም ሆነ ሊቀንስ ይችላል።
- መ/ቤቱ የዕቃው ጥራት በባለሙያና በስፖርተኞች ሲረጋገጥ ብቻ ውል ተዋውሎ ማስቀጠል የሚቻል ይሆናል።
- በጨረታው ማስታወቂያው ላይ ያልተገለጹ ተጨማሪ ማሳሰቢያዎች በጨረታ ሠነዱ ላይ የሚገለጹ ካሉ እንደ ማስታወቂያ የሚያገለግል ስለሆነ ሁሉም ተጫራች ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል።
- ክለብ ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈተው ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን ሲሆን በዕለቱ 9፡00 የጨረታ ሳጥን የሚታሸግ ሆኖ በዕለቱ 9፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የማይገኙ ከሆነ የጽ/ቤቱን ስራ አያስተጓጉልም። የተጫራቹ ተወካይ የሚቀርብ ከሆነ ስለ ውክልናው ህጋዊነት የሚገልጽ መረጃ ይዘው መቅረብ ይኖርበታል።
- የክለብ ጽ/ቤቱ አድራሻ በአ/ምንጭ ሀለገብ ስታዲዬም የሚገኝ ሲሆን ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡_ 0468813605 ይደውሉ።
የአርባ ምንጭ ከተማ እግር ኳስ ክለብ
