የጉምሩከ ኮሚሽን ጅጅጋ ቅጽ/ቤት በኮንትሮባድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጉምሩከ ኮሚሽን ጅጅጋ ቅ ጽ/ቤት በኮንትሮባድ የተያዙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሽከርካሪዎች ከ17/12/2014 ጀምሮ በማየት እና ከዚህ ቀጥሎ የተገለፁትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ቅ/ጽ/ቤቱ ይገልፃል። በጨረታው ላይ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የዘርፍ ንግድ ፍቃድ ያለው እና የዘመኑን ግብር የከፈለ እንዲሁም የነዋሪነት መታወቂያ ያለው ማንኛውም ኢትዮጵያዊ
- የመጫረቻውን 5% (ፐርሰንት) ማስያዝ የሚችል፤
- ለግልፅ ጨረታ ቅ/ፅ/ቤቱ ካስቀመጠው መነሻ ዋጋ ተነስቶ ዋጋ በመሙላት በተቀመጠው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቹ በጨረታው አሸንፎ የገዛውን ዕቃ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን የሚረከብ መሆን አለበት።
- ዕቃዎቹን አሸንፎ የገዛ ተጫራች የሚፈለግበትን ዋጋ ወዲያውኑ ከፍሎ በ05 ቀን ውስጥ ካልተረከበ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
- በጨረታው ያላሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጅጅጋ ቅርንጫፍ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ አሰርቶ ማምጣት አለበት።
- አሳማኝ የሆነ ምክንያት ከተገኘ እና በመ/ቤቱ ተቀባይነት ካላገኘ ጨረታውን መሰረዝ ይችላል።
- ማንኛውም ተጫራች ዕቃዎቹን ካሸነፉ በኋላ ከጅጅጋ ውጪ ለማጓጓዝ ቢፈልግ እንደቦታው ርቀት በቀነ ገደብ መሸኛ ሊሰጣቸው ይችላል።
- ተጫራቹ ዕቃዎቹን አሸንፎ ከተረከበ በኋላ መሸኛ ሳይዝ የትም ቦታ ቢያዝ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
- ተጫራቾች የሞሉትን የጨረታ ሰነድ ነሐሴ 19/12/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 3፡45 በጅግጅጋ ጉ/ኮ/ ቅ/ጽ/ቤት በተዘጋጀ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ጨረታው 3፡45 ተዘግቶ በ19/12/2014 ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
N.B. አሸናፊው ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) 15% ፐርሰንት የሚከፍል መሆኑ ይታወቅ።
በጉምሩክ ኮሚሽን የጅጅጋ ቅ/ጽ/ቤት
