Tender Detail

Tender Details

  • Deadline02 Oct 2022, 11:13 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሃገር ውስጥ የተለያዩ መዳረሻዎች የስኳር ጭነት ለማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር- ESLS/MM/NCB/06/2015

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከጅቡቲ ወደብ ወደ ሃገር ውስጥ የተለያዩ መዳረሻዎች የስኳር ጭነት ለማጓጓዝ የትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ የተሰማራችሁ የጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
  2. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስhር ወረቀት የትራንስፖርት ማህበራትን አይመለከትም፤
  3. በዘርፉ የተሰማሩ ሁሉም ድርጅቶች ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የተሰጠ የታደሰ የጭነት አገልግሎት የደረጃ ብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት /ሠርተኬትየግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬት
  4. ጊዜው ያላለፈበት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችሉ የግብር አከፋፈል ምስክር ወረቀት ማስረጃ (Tax clearance certificate/
  5. ተጫራች ድርጅቶች የንግድ ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሽግ ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራች ድርጅቶች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 50,000 (ሃምሳ ሺ ብር ብቻ) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ጋራንቲ “የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት" በሚል ስም በማሰራት ከቴክኒካል ፖስታው ጋር ወይንም ለብቻው በማቅረብ መጫረት ይችላሉ።
  7. የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የማይመለስ ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል ለገሃር በሚገኘው ሁለገብ ሕንጻ 3ኛ ፎቅ ላይ ከሚገኘው የፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
  8. ጨረታው “በኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት" ዋና መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ፖስታው ይከፈታል።
  9. ከጨረታ መክፈቻው ቀንና ሰዓት በኋላ ዘግይቶ የሚመጣ የጨረታ ሠነድ ተቀባይነት የለውም።
  10. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 011 554 9781/86

የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ

አገልግሎት ድርጅት

Save Tender