Tender Detail

Tender Details

  • Deadline04 Sep 2022, 10:54 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

የግራር ጃርሶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የፅህፈት መሣሪያዎች ፣ የተለያዩ የፅዳትና አላቂ እቃዎች ፣ ጥቃቅን የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣ ቋሚ ዕቃዎችን ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ፣ የመኪና ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ግ/ጨ/ ቁጥር 01/2015

የግራር ጃርሶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙት ሴከተር መ/ቤቶች ለ2015 ዓ.ም. የበጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የተለያዩ

  1. የፅህፈት መሣሪያዎች፣
  2. የተለያዩ የፅዳትና አላቂ እቃዎች፣
  3. ጥቃቅን የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች፣
  4. የደንብ ልብስ፣
  5. ቋሚ ዕቃዎችን፣
  6. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣
  7. የመኪና ጎማዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፦

  1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ የተሰማሩበትን የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት (TIN) ያላቸው፣ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው የእቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ተመዝግበው (ppf) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 100፡00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከመ/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃ ሞዴል (Brand Name) ባልተገለፀበት ቦታ በጨረታው ዝርዝር ላይ መግለፅ አለባቸው።
  5. አቅራቢዎች በእያንዳንዱ የዕቃ ዝርዝር ማቅረቢያ ሠንጠረዥ ውስጥ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋውን እንዲሁም ቀን ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ማስፈር ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች እቃዎቹን የሚሸጡበትን ዋጋና አይነት በመለየት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው ተከታታይ የሥራ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማስገባትና ናሙናውንም በማቅረብ በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያው ቀን በ8፡30 ተጫራችች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወረዳው 1ኢ/ት/ጽ/ቤት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
  7. ከጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  8. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን ከመደበኛ የስራ ቀናት ውጪ ከዋለ ቀጣዩ የስራ ቀን እንደ ጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን ይቆጠራል።
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላለ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን /VAT/ እና ሌሎችንም ያጠቃለለ መሆን አለበት።
  10. ተጫራቾች የተመረጡትን የእቃ ናሙና ማቅረብ ግደታ አለባቸው። ናሙና የማያቀርብ ተጫራች መወዳደር አይቻልም።
  11. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የቀረበው የጨረታ ሰነድ መቀየር ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራሱን ማግለል አይቻልም።
  12.  የተሰረዘና የተደለዘ ማስረጃና ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  13. የጨረታው አሸናፊዎች የታዘዙትን ዕቃዎች በራሳቸው ወጪ ግራር ጃርሶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  15. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም። ተጫራቾች እቃዎቹን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ገብቶ ውል በገባው ጊዜ ውስጥ አጠናቀው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • አድራሻ፡_ በጎጃም መንገድ ከአዲስ አበባ 112 ኪ.ሜትር ፍቼ ከተማ ቴሌ ፊት ለፊት ነው።
  • ለበለጠ መረጃ፡_ በስልክ ቁጥር 011 135 0558 ወይም 011 160 9470 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

የግራር ጃርሶ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት

Save Tender