የመከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ዓይነት የግርግዳ እና ኳርትዝ ቀለሞች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/BM/101/2022
የመከላከያ ኮንስትራከሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ አፓርትመንት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከታች በሠንጠረዥ እና በጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የተለያዩ ዓይነት የግርግዳ እና ኳርትዝ ቀለሞች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
No |
Item |
Unit |
Quantity |
|
1 |
White Plastic paint |
Gallon |
3,369 |
|
2 |
Plastic paint Broken White |
Gallon |
8,752 |
|
3 |
White Synthetic Paint |
Gallon |
2,094 |
|
4 |
Quartz Paint, 40 |
Gallon |
52,480 |
|
5 |
Quartz Paint, 117 |
Gallon |
63,964 |
|
6 |
Quartz Primer |
Gallon |
8,951.25 |
ስለሆነም:-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- 3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ስዓት ወሎ ሰፈር አካባቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ እና አቅርቦት አስተዳደር መመርያ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ ጳጉሜን 02/2014ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡ 00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ጳጉሜን 02/2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 440 3434/33
ማዞሪያ 011 442 2270/71/72
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ.011 440 0471/011 442 0746
ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
www.dce-et.com/Email:-Info@dce-et.com
መከላከያ ሚኒስቴር የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
