የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ባለ 2ፎቅ ህንጻ /G+2/ የሆነውን የጽ/ቤቱን ህንፃና የምድረ-ግቢ ፅዳት አገልግሎት እና ለዕ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት እቃዎች ፣ የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አፋር 01/2015
የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉሉ የቢሮ የተለያዩ ክፍሎችን የተሟላ ማቴሪያል አቅርቦ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ
- ባለ 2ፎቅ ህንጻ /G+2/ የሆነውን የጽ/ቤቱን ህንፃና የምድረ-ግቢ ፅዳት አገልግሎት እና
- ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ የጽዳት እቃዎች ፤
- የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርባቸዋል።
- በዘርፉ የታደሠ ንግድ ፈቃድ
- ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ስራ ፈቃድ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት
- መንግስት አገልግሎት ሰጭነት የተመዘገበ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ሰርተፍኬት ያለው
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ስራዎች/አገልግሎት/ 1% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ (C.P.O) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋልየጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ይመለስላቸዋል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 01 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ በሚሰጠው አገልግሎት ወይም የጽ/ቤቱን ህንፃና የምድረ-ግቢ ፅዳት አገልግሎት ዋጋ በግልጽና በማያሻማ መልኩ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ከዚህ መመሪያ ጋር በተያያዘ ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ የወር እና የዓመት ዋጋውን ከነሻቱ ሞልቶ ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልቶ በሠም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናል እና ኮፒ በመለየት በተወሰነው ጊዜ ውስጥ ሠመራ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ምድር ላይ በሚገኘው ቢሮ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ላሉት ተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ እና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት የሚዘጋ ሆኖ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል።ሆኖም ግን የመክፈቻው ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል። እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምክኒያት በሚከፈትበት ግዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
ሠመራ
