የቶሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2015 ዓ.ም. በወረዳዉ ለሚገኙት የመንግስት መስሪያ ቤቶች ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ አላቂ እቃዎች (ስቴሽነሪ) የመኪና እና የሞተር ጎማዎች ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ግዥ እና ስፌትን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የቶሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2015 ዓ.ም. በወረዳዉ ለሚገኙት የመንግስት መስሪያ ቤቶች
- ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- አላቂ እቃዎች (ስቴሽነሪ)
- የመኪና እና የሞተር ጎማዎች፣
- የጽዳት እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ ግዥ እና ስፌትን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን።
- ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ የሚያቀርብ እና የዘኑን ግብር የከፈሉበትን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ።
- በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ኮፒውና ኦርጅናሉን በማቅረብ ስም ፊርማና አድራሻቸውን ማስቀመጥ አለባቸው።
- በጨረታ ሰነድ ከተገለፀው የዕቃ ፕሮፖዛል ውጭ ተመሳሳዩን ማቅረብ እንደማይቻልና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ በስህተት ቢቀርብ መቀየር የሚችል።
- የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድረገዉ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 3/12/2014 ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11:30 ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚችሉ ሲሆን ጨረታዉ በ15ኛው ቀን 23/12/2014 ከቀኑ 11፡30 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 24/12/ 2014 ከጠዋቱ 3፡00 በቢሮ ቁጥር 7 ይከፈታል።
- የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) 5000.00 (አምስት ሺህ) ወይም በካሽ ከጨረታው ሠነድ ጋር ብር 5000.00 (አምስት ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተረጋገጠ በኃላ የውል ማስከበሪያ ጠቅላላ ካሸነፈው ዕቃ የሚለስ 10% ማስያዝ አለበት
- ያሸነፈውን ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል።
- ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተረጋገጠና ዕቃውን ጽ/ቤቱ ድረስ በራሳቸዉ ወጪ አምጥተው ካስረከቡ በኋላ ክፍያዉ ይፈፀማል።
- የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00 (መቶ ብር) ለአንድ ሎት በቶሌ ወረዳ ገቢዎች ባለስልጣን ፅ/ቤት ከፍሎ መግዛት ይችላሉ።
- በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር (suppliers list) ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻችን፡- የቶሌ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት ፤ አ/አ-አስጎሪ-ባንቱ በሰበታ መስመር 80 ኪሜ ከአ.አ
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0912 34 75 54/0945 73 73 02/0911 72 95 89 /011 313 0273 መደወል ይችላሉ፡።
በደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን የቶሌ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት
