የምስራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ውስጥ ለሚገኙት የህግ ታራሚዎች ምግብ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የምስራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ውስጥ ለሚገኙት የህግ ታራሚዎች ምግብ አቅርቦት መስከረም 1/2015 እስከ ታህሳስ 30 2015 ዓ.ም. ለ 4 (አራት/ ወር በሚቆይ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
በዚሁ መሰረት ማንኛውም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ
- የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ወይም ቢሮ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የዘመኑ የስራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና አግባብነት ያለው 2014 የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርTIN የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 30(ሰላሳ ብር) በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከዞን ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤቶች በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዳቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዞን ማረሚያ ቤት እስ/ፅ/ቤቶች ለዚሁ የተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከ መቶ ሁለት 2 /ፐርሰንት/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ CPO/ እና የምግብ እህል ናሙና ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
- .ጥቃቅን እና እነስተኛ ንግድ ተደራጅተው የበሰለ ምግብ ለማቅረብ የሚቀርቡ ማህበራት ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 14 ለተከታታይ ቀን በአየር ላይ ውሎ 15 ቀን በስራ ቀን ከረፋዱ በ 4፡00 ሰአት በዞን ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም የህግ ታራሚ ኮሚቴዎችና የመ/ቤቱ የጨረታ ኮሚቴ አባላት በተገኙብት ይከፈታል።
- የዞኑ ማረሚያ ቤት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሱ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተዘጋጀ ማብሰያ ቤት ውስጥ ምግብ አብስሎ ማቅረብ የሚችል ማረሚያ ቤቶች የሚገኙበት ከተማ
|
ተ.ቁ |
የዞን ማረሚያ ቤት |
የሚገኝበት ከተማ |
|
1 |
የምስራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት |
ጊንር |
ለበለጠ መረጃ በስልከ ቁ.ጥ 022 664 0031 /0913 56 25 24/0913 72 68 90 ደውለው መጠየቅይችላሉ
የኦሮሚያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የምስራቅ ባሌ ዞን ማረሚያ ቤት አስ/ፅ/ቤት
ጊንር
