ዲቦራ ፋውንዴሽን ለአራት አመት ተከታታይ ውል በየአመቱ የሚታደስ ሆኖ ሂሳቡን በውጪ ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
ዲቦራ ፋውንዴሽን በምዝገባ ቁጥር 4230 መሰረት የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው። ፋውንዴሽኑ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ህፃንት መብታቸው ተጠብቆ እና እንደማንኛውም ዜጋ ለሃገራቸው የሚጠቅሙ ዜጎች እንዲሆኑ መርዳትን አላማው አድርጎ የተቋቋመ ድርጅት ነው። ፋውንዴሽናችን ለአራት አመት ተከታታይ ውል በየአመቱ የሚታደስ ሆኖ ሂሳቡን በውጪ ኦዲተሮች ማስመርመር ይፈልጋል።
በመሆኑም በመስኩ የታደሰ የሥራ ፈቃድና ሌሎች ተያያዥ ሕጋዊ ማስረጃዎችን እና በተጠቀሰው ኦዲት ሥራ ላይ ከዚህ ቀደም የሠሩ ስለሆናቸው የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ወይም ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ባለሙያዎች መወዳደር ይችላሉ። የጥናትና የመረጃ ማሰባሰብ ሥራው እስከ ነሐሴ 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ተጠናቆ በፋውንዴሽናችን በአካል በመቅረብ ተወዳዳሪዎች የሚሰሩበትን የዋጋ ዝርዝር በፖስታ አሽገው ማስታወቂያው በጋዜጣ ለመጀመሪያ ጊዜ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሥራ ሰዓት በመምጣት ማስገባት ይችላሉ።
- ማሳሰቢያ፡- ፋውንዴሽኑ ሌላ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም።
ለተጨማሪ መረጃ
- በስልክ ቁጥር +251 92 019 1372 ወይም +251 93 303 8964 ደውለው ይጠይቁ
ዲቦራ ፋውንዴሽን
