በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የደሴ ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ ለ2015 ዓ.ም. የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች ፣ ቋሚ የቢሮ እቃ (ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸር) ፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣ የተለያዩ ሕትመቶች ፣ የመኪና ዘይትና ቅባት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልጽ የብሔራዊ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቀጥር-001/2015
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የደሴ ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ ለ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን ከዚህ በታች በተዘረዘረው ምድብ መሰረት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ምድብ 1 የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣
- ምድብ 2 የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች ፣
- ምድብ 3 ቋሚ የቢሮ እቃ (ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸር) ፣
- ምድብ 4 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ ለ1 ዓመት ውል በመያዝ
- ምድብ 5 የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች ፣
- ምድብ 6 የደንብ ልብስ ፣
- ምድብ 7 የተለያዩ ሕትመቶች ጨረታ ለ1 ዓመት ውል በያዝ
- ምድብ 8 የመኪና ዘይትና ቅባት
ስለዚህ ድርጅትዎ የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልቶ መወዳደር እንዲችል ይጋብዛል።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
- ግዢ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- በአቅራቢነት የተመዘገቡ፤
- ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ (በሎት ነው) ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከ5/12/2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 20/12/2014 ዓ.ም. 4፡00 ሰአት ድረስ ደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር-05 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ምድብ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለየምድቡ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ5/12/2014 ዓ.ም. እስከ 20/12/2014 ዓ.ም. 4፡00 ሰአት ድረስ ደሴ ከተማ አስ/ር ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ20/12/2014 ዓ.ም. 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዛው ቀን 4፡30 በደሴ ከተማ አስ/ር ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ከስራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደሴ ከተማ አስ/ር ገንዘብ መምሪያ ግ/ን አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-8629 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የደሴ ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ
