በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት በጉራጌ ዞን የም/አ/ወ/ፋይናንስ/ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት ስቴሽነሪ ፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የመኪናና የሞተር ሳይክል ጎማዎች ፣ ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ለመጀመያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 0001
በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት በጉራጌ ዞን የም/አ/ወ/ፋይናንስ/ጽ/ቤት በ2015 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ
- ሎት አንድ ስቴሽነሪ
- ሎት ሁለት የጽዳት እቃዎች
- ሎት ሶስት የመኪናና የሞተር ሳይክል ጎማዎች
- ሎት አራት ጀነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ ብር 10,000 (አስር ሺ) ፤ ለሎት ሁለት 5,000 (አምስት ሺ) ፤ ለሎት ሶስት 10,000 (አስር ሺ) ፤ ለሎት አራት 10,000 (አስር ሺ) በም/አ/ወ/ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሰራት ይጠበቅባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው በኦሪጂናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በም/አ/ወ/ገ/ባ/ቅ/ጽ/ቤት የማይመለስ 50 (ሃምሳ ብር) በመክፈል ከምሁርና አክሊል ወረዳ ፋ/ፅ/ቤት ግዢ ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ መዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የእያንዳንዱ ሎት ኦርጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊው ዕቃዎቹን እስስከ ቢሮአችን የሚያጓጉዝ ወጪ በራሱ ይሸፍናል።
- ጨረታው በአስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ታሸጎ 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይተላለፋል።
- ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ፡- 011 343 0173/011 343 0614 ይደውሉ።
በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሐዋሪያት
