Tender Detail

Tender Details

  • Deadline26 Aug 2022, 4:43 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የደሴ ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ ለ2015 ዓ.ም. የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች ፣ ቋሚ የቢሮ እቃ (ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸር) ፣ የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣ የተለያዩ ሕትመቶች ፣ የመኪና ዘይትና ቅባት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


ግልጽ የብሔራዊ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቀጥር-001/2015

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የደሴ ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ ለ2015 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አቅርቦቶችን ከዚህ በታች በተዘረዘረው ምድብ መሰረት በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. ምድብ 1 የተለያዩ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ፣
  2. ምድብ 2 የተለያዩ የጽዳት ዕቃዎች ፣
  3. ምድብ 3 ቋሚ የቢሮ እቃ (ኤሌክትሮኒክስና ፈርኒቸር) ፣
  4. ምድብ 4 የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች ፣ ለ1 ዓመት ውል በመያዝ
  5. ምድብ 5 የተለያዩ የተሽከርካሪ ጎማዎች ፣
  6. ምድብ 6 የደንብ ልብስ ፣
  7. ምድብ 7 የተለያዩ ሕትመቶች ጨረታ ለ1 ዓመት ውል በያዝ
  8. ምድብ 8 የመኪና ዘይትና ቅባት

ስለዚህ ድርጅትዎ የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልቶ መወዳደር እንዲችል ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤
  2.  የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤
  4. ግዢ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  5. በአቅራቢነት የተመዘገቡ፤
  6. ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ (በሎት ነው) ከላይ ከተራ ቁጥር 1-5 ድረስ የተዘረዘሩትን የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ከ5/12/2014 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ 20/12/2014 ዓ.ም. 4፡00 ሰአት ድረስ ደሴ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር-05 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ምድብ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለየምድቡ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋናና ቅጂ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ5/12/2014 ዓ.ም. እስከ 20/12/2014 ዓ.ም. 4፡00 ሰአት ድረስ ደሴ ከተማ አስ/ር ገንዘብ መምሪያ ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ20/12/2014 ዓ.ም. 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዛው ቀን 4፡30 በደሴ ከተማ አስ/ር ገንዘብ መምሪያ ግዥ ንብረት አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ይከፈታል። የጨረታው መክፈቻ ቀን ከስራ ቀን ውጪ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደሴ ከተማ አስ/ር ገንዘብ መምሪያ ግ/ን አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-8629 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን አስተዳደር የደሴ ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ

Save Tender