Tender Detail

Tender Details

  • Deadline25 Aug 2022, 4:43 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Other Sales

ዳታ ኮንስትራክሽን በህግ እየፈረሰ ያለ ደረጃ አንድ ኮንስትራክሽን ድርጅት ሲሆን የድርጅቱን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ መለያ ቁጥር ዳኮ/02/2014

ዳታ ኮንስትራክሽን በህግ እየፈረሰ ያለ ደረጃ አንድ ኮንስትራክሽን ድርጅት ሲሆን የድርጅቱን ንብረቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

  1.  ጨረታው በንግድ ሚኒስቴር እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መመሪያ ላይ በተጠቀሰው የግልጽ ጨረታ ሂደት መሰረት ይከናወናል።
  2. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፣ የሚፈለግባቸውን የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልጽ ደብዳቤ፣ የግብር ከፋይነት ሠርተፍኬት ፣ እና ሌሎች መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋናው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በኦሮሚያ ባንክ ሂሳብ ዳታ ኮንስትራክሽን ሂሳቡ በመጣራት ላይ ያለ በሚል ስም በአካውንት ቁጥር 1510489360001 በማስገባት የከፈሉበትን አድቫይስና ንግድ ፈቃዳቸውን በስልክ ቁጥር 0932071428 ቴሌግራም በመላክ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ በጨረታ ያስገቡትን 25 መቶኛ ቢያንስ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ቅድመ ሁኔታ ባላካተተ የባንከ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህም ከዋናው የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር ወይም ለብቻው ማቅረብ ይቻላል።
  5. አድራሻ ዳታ ኮንስትራከሸን ኃ/የተ/ወ/የግል ማህበር በህግ እየፈረሰ ያለ ድርጅት ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911-05-99-43/0912-07-09-60 መጠየቅ ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተካተቱትን መመሪያዎች ማሟላት ይገባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ይህ ጨረታ ከወጣ በ15 ቀን በኋላ ነሐሴ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡30 ይከፈታል።
  8. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሂሳብ አጣሪ

ስልክ ቁጥር 0932-07-14‐28/0911-05-99-43

ዳታ ኮንስትራክሽን ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ

Save Tender