Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Aug 2022, 4:33 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ይዞታ ስር ያሉትን የቀላል ተሽከርካሪዎችን ጥገናና እድሳት በ2015 በጀት ዓመት የጋራዥ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የጥገና አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

በመከላከያ ሰራዊት ፋውንዴሽን ይዞታ ስር ያሉትን የቀላል ተሽከርካሪዎችን ጥገናና እድሳት በ2015 በጀት ዓመት የጥገና አገልግሎት የሚሰጡ በአዲስ አበባ ክልል ውስጥ የሚገኙ የጋራዥ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የጥገና አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶችን በጨረታ እንዲሣተፉ ይጋብዛል።

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TIN/፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የአቅራቢነት የምዝገባ ሠርተፊኬት የኢንሹራንስ ምስክር ወረቀት እንዲሁም ለግብር ከፋይ የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቂርቆስ ከ/ከተማ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን በሚገኘው በፋውንዴሽኑ ዋና መ/ቤት ኮርፖሬት ግዥ ቢሮ ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል ሠነዱን ማግኘት ይችላሉ። ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋውንዴሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድን ማስከበሪያ ዋስትና በማስያዝ በጨረታ ሰነድ ላይ በተገለጸው መሰረት በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ ማስገባት አለባቸው።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ዋስትና በመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ስም ብር 20,000.00 በባንክ በተረጋገጠ የከፍያ ማዣ (CPO) ወይም የባንከ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸ።
  6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ

መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን

ከቄራ ወደ ሜክሲኮ በሚወስደው መንገድ ላንድማርክ ሆስፒታል ጎን

ስ.ቁጥር 011 557 2734/ፖ.ሳ.ቁ.5680

መከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን

አዲስ አበባ

Save Tender