የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወሪት ይታጠቁ ቦጋለ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ሄኖክ ቦጋለ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/19605 በ5/11/2013 ዓ/ም እና በ216699 በ27/12/2013 ዓ.ም በ7/8/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአራዳ |ከተማ ወረዳ 04 የቤት ቁጥር 390 የሆነው ጅምር ቤት የቦታው ስፋት 209 ካ/ሜ በቁጥር አ/7/29/80n/o የተመዘገበ ካርታ ያለው የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 3,321,361.70 ሦስት ሚሊዮን ሦስት መቶ ሃያ አንድ ሺ ሦስት መቶ ስልሳ አንድ ብር ከሰባ ሳንቲም ሆኖ) የትራንዛክሽን ታስ ገዥ የሚከፍል ሆኑ ታውቆ ጥቅምት11 ቀን 2015 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡ የተጫራቾች ምዝገባ 4፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬከቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CRO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ 15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታhስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
