Tender Detail

Tender Details

  • Deadline23 Aug 2022, 11:45 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Food Items And Drinks

የምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በኦሮሚያ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የምስራቅ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት ቁጥር-3 ውስጥ ለሚገኙት ለ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ፍቃድ ያላቸውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በኦሮሚያ ማረሚያ ቤት ኮምሸን የምስራቅ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት ቁጥር-3 ውስጥ ለሚገኙት ለ2015 ዓ.ም ባጀት ዓመት ለህግ ታራሚዎች የበሰለ ምግብ ለማቅረብ ፍቃድ ያላቸውን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ እንድትሳተፉ ተጋብዘዋል።

  1. በዘርፉ የታደስ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የ2014 ዓ.ም የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ እና በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘቡ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ሰነድ 27/11/2014 ዓ.ም እሰከ 17/12/2014 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለው ከምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ከፎቅ ቁጥር 1 መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ከለፉት ዓመታት በአቅራብነት ችግር ያልፈጠሩ ጥሩ የአቅራቢነት ባህሪ ያለቸው መሆኑ ከመንግስት መ/ቤት የምስጋና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ማስከበሪያ ዋስትና Bid Bond (CPO) 5,000 ( አምስት ሺህ ብር) ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ምግብ ጥራት ያለውና ደረጃውን የጠበቀ መሆን አለበት።
  6. ተጫራቾች የምግቡን ዋጋ ዝርዝር የተጠየቀውን “Specification" ሳይለውጡ የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ላይ ዋጋውን በመሙላት ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና አድራሻቸውን በማሰፈርና ማህተም በማድረግ የጨረታ ዶክመንታቸውን ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖሰታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 17/12/2014 ዓ.ም ድረስ ከፎቅ ቁጥር 1 በተዘጋጀው ሣጥን ጨረታውን ከመዘጋቱ ከ04፡00 ሰዓት በፊት ማሰገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነድ ጋር የተሰጠውን መመርያ (መሳፈርቶች) በኦሮምኛ ቋንቋ ተያይዞ የቀረበ መመርያ መከተል አለባቸው።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ኪሎቻቸው በተገኙበት 18/12/2014 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም መኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
  9. የጨረታው ሣጥን ከታሸ ወይም ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  10. የጨረታ አሸናፊ ተጫራቾች ምግብን ከውል ሰጪው መ/ቤት ጋር በሚደረገው የውል ስምምነት መሠረት ነቀምት በሚገኘው በውል ሰጭው ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።
  11. ተጫራቾች በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በተዘጋጀ ማብስያ ቤት ውስጥ ምግብ አብስሎ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።
  12. መ/ቤታችን በሚያወዳደረው ጠቅላላ የዋጋ ብዛት ላይ እንደየአሰፈላጊነቱ 20% መጨመርና መቀነስ ይችላል።
  13. ተጫራቾች ምግብ አሸንፈው ለማቅረብ ሲዋዋሉ ከሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  14. ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸ ከአምስት ቀን በኃላ በውል ሰጪው መ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት የውል ስምምነት የመፈፀም ግደታ አለበት።
  15. ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የምስራቅ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ስልከ፡ 057 660 2207/057 661 7438 / 34/ 1042

በኦሮሚያ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የምስራቅ ወለጋ ዞን ማረሚያ ቤት
    

Save Tender