Tender Detail

Tender Details

  • Deadline17 Aug 2022, 11:16 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር HDPE pipe በ12 ሜትር በሃይቤድ ወደ ተለያዩ አማራ ክልል ቦታ የማጓጓዝ ስራ አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ለመግዛት ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

የጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከታች የተዘረዘረውን አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ለመግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ

ሎት

የእቃው አይነት

የጨረታ ማስከበሪያ

የማቅረቢያ ጊዜ

1

ሎት 1

HDPE pipe በ12 ሜትር በሃይቤድ ወደ ተለያዩ አማራ ክልል ቦታ የማጓጓዝ ስራ

30,000.00

 

 ስለዚህ ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራና በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ሀይቤድ ያላችሁ ድርጅቶች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድረ-ገጽ www.tisisat.com ላይ ማገኘት ትችላላችሁ።

የተጫራቾች መመሪያ፡-

  1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር ከፍለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ/የደረቅ ጭነት ፈቃድ እና የTIN ሰርተፊኬት፣ በዘርፉ ለመሰማራት የተሰጣቸውን ፈቃድ እና ተያያዥነት ያላቸውን የመልካም ስራ አፈፃፀም ማስረጃዎች ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ 10፡30 ሰዓት ባህርዳር ከተማ አባይ ማዶ ቴዲ የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ጎን በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ተጫራቾች እና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተዘግቶ ይከፈታል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ድረ-ገጽ www.tisisat.com ማግኘት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች (ጨረታ ማስከበሪያ በሰንጠረዥ የተመለከተውን ገንዘብ በC.PO ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ ለገዥ የሚከፈል (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በኮፒ እና ኦርጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራች  ድርጅቶች ለሚያቀርቡት ዋጋ ነጠላ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ በትhክል ሞልተው በግልፅ ማስቀመጥ አለባቸው።
  6. ይህ ጨረታ በኩባንያችን የግዥ መመሪያ ነሐሴ/2013/ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል።
  7.  ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ ከተገለፀው መጠን 25% ቢጨምር ወይም ቢቀንስ የጨረታ አሸናፊው ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
  8. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በጽሁፍ hተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋውን 10 % የውል ማስከበሪያ ያለቅድመ ሁኔታ ለገዥ የሚከፈል (unconditional Bank Guarantee) በማሰራት ውል የመያዝ ግዴታ ይኖርበታል።
  9. የማቅረቢያ ጊዜ ከላይ በሰንጠረዥ በተገለጸው መሰረት መሆን አለበት። የአቅራቢዎች አስገዳጅ ሁኔታ ካልተፈጠረ በስተቀር ዋጋ ቢያንስ ለ90 ቀናት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ፀንቶ መቆየት አለበት።
  10. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም ወይም ጨረታውን በሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. ማሳሰቢያ፡- ውድድሩ የሚሄደው በሎት ሳይሆን በእያንዳንዱ የማጓጓዥያ ቦታ በሚሰጡት ነጠላ ዋጋ በሚሞሉት ዋጋ መሰረት ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን 058-220-48-26/0583202548/

በፋክስ ቁጥራችን 0582204830 ይጠቀሙ።

ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች ኃ/ተ/የግ/ማህበር

Save Tender