የኢትዮጵያ የአንጎልና ህብለ ሰረሰር ቀዶ ጥገና ባለሞያዎች ማህበር የ2019/2020 በግሪጎሪያን አቆጣጠር በጀት ዓመት ሂሳብ ለማስመርመር (ኦዲት) ለማስደረግ ይፈልጋል
የኦዲት ሥራ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የአንጎልና ህብለ ሰረሰር ቆዶ ጥገና ባለሞያዎች ማህበር በበጎ አድራጎት ድርጅቶች ማህበራት አዋጅ መሰረት የኢትዮጵያ የሙያ ማህበር ሆኖ ጥቅምት 24,2009 ዓ.ም. በመዝገብ ቁጥር 3716 ከኤጄንሲው ፈቃድ አግኝቶ የሚሰራ ድርጅት ነው። ማህበሩ የ2019/2020 በግሪጎሪያን አቆጣጠር በጀት ዓመት ሂሳብ ለማስመርመር /ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶችን የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
መሟላት ያለባቸው መስፈርቶችም፡-
- የንግድ ፈቃድ ያላቸው
- በሙያ ብቃትና ሕጋዊነት ታውቀው በመንግስት የተመዘገቡ
- የዘመኑን ግብር ከፍለው በ2013 ዓ.ም. በጀት ዓመት ፈቃዳቸውን ያሳዱ
- የኦዲቲንግ የሥራ ልምድ ያላቸው
- የተመሰከረለት የሂብ አዋቂዎች ሠርተፊኬት ያላቸው
- የታክስ መለያ ቁጥር ያላቸው መሆን አለባቸው
- ተወዳዳሪዎች ለአገልግሎት የምትስከፍሉትን ዋጋና ስራውን ሰርታችሁ የምታስረክቡበትን ጊዜ በመጥቀስ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የሙያ ደረጃችሁንና ህጋዊነታችሁን የሚገልጹ ማስረጃዎች በማያያዝ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ እንድታመለክቱ እናስታውቃለን።
አድራሻ፤- በአፍሪካ ሕብረት ዋና መ/ቤት ዋናው የመግቢያ በር ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ሐኪሞች ማሕበር ቅጥር ግቢ ውስጥ
ስልክ +251 91 168 2063/ 0912 14 31 10
የኢትዮጵያ የአንጎልና ህብለ ሰረሰር ቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር
