የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2014 በጀት ዓመት አገልግሎታቸውን የጨረሱ ጋዜጦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስወገድ ይፈልጋል
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
መ/ቤታችን በ2014 በጀት ዓመት አገልግሎታቸውን የጨረሱ ጋዜጦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በሽያጭ ማስወገድ ይፈልጋል።
በመሆኑም፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይቻላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውል ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር) ብቻ CPO ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቢድ ቦንድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው በ6ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል።
- የጨረው አሸናፊ አሸናፊነቱ በፅሑፍ ከተገለፀለት በኋላ በቀን ውስጥ ውል ተዋውሎ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ ክፍያ ፈጽሞ ዕቃውን ሙሉ በሙሉ ማንሳት ያለበት ሲሆን በተባለው ጊዜ ባያነሳ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ይወረስበታል።
ድርጅታች ጨረታውን አስመልክቶ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 0118-11 12 89
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
