Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 Aug 2022, 5:47 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cargo Vehicle

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ከተለያዩ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የገዛውን እና መንግስት ባስቀመጠው የስርጭት አቅጣጫ መሰረት ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በተለያዩ ቅርንጫፎቹ በኩል የሚያሰራጨውን ሲሚንቶ ከሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የሚያጓጉዙ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል ማሰራት ይፈልጋል


የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት

የጭነት አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/14

ድርጅታችን ከተለያዩ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች የገዛውንና መንግስት ባስቀመጠው የስርጭት አቅጣጫ መሰረት ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በተለያዩ ቅርንጫፎቹ በኩል የሚያሰራጨውን ሲሚንቶ ከሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የሚያጓጉዙ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ ዓመት በሚቆይ ውል ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች

1.በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ ሠርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ክሊራንስ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርተፍኬት ያላቸው መሆን ይገባቸዋል።

2. ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ቢስ መብራት አካባቢ ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ ሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  • 3.1 ከዚህ ቀደም ለሌላ ጨረታ የተያዘ ሲ.ፒ.ኦን ለዚህ ጨረታ እንዲያዝ ማድረግ አይቻልም።
  • 3.2 ተጫራቾች በጨረታ መመሪያው ላይ የሚቀመጡትን ህጎች በሙሉ በማክበር ግዴታ አለባቸው።

4. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውንና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ ሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ።

5. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን (ሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ.ም.) ከቀኑ 8፡05 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን ውሳኔዎች የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ

በስልክ ቁጥር 011 369 2647 | 69-2439

Save Tender