Tender Detail

Tender Details


የዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አ.ማ. ለጎንደር ጋርመንት ፋብሪካ የማሽንና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሥራ ለማሠራት ሥራውን የሚሠራ ድርጅት ወይም ግለሰብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል


ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: NCB-AID 01/2014

የዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አ.ማ. ለጎንደር ጋርመንት ፋብሪካ የማሽንና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ ሥራ ለማሠራት ሥራውን የሚሠራ ድርጅት ወይም ግለሰብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የአገልግሎት ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

 ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 10001 62 58 91 84 ገቢ በማድረግ በተጫራቹ ድርጅት (ግለሰብ) ስም የገባውን የባንክ ኦርጅናል ሰነድ በማቅረብ ባህር ዳር ቀበሌ 8 በሚገኘው አማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ግቢ ውስጥ 1ኛ ፎቅ የአክሲዮን ማህበሩ ቢሮ ወይም አ/አ ቅ/ጽ/ቤት አራት ኪሎ አካባቢ ከሚገኘው አልማ ህንፃ ላይ በሚገኘው ጽ/ቤታችን ማግኘት ይችላሉ።
  4. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለ20 ተከታታይ ቀናት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል።
  5. ኩባንያው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. ኩባንያው በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን ሥራዎች 50% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ብለው ለየብቻ በማሸግ እንዲሁም ዋና እና ቅጂ ብለው በታሸገ ፖስታ መመለስ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የአገልግሎት ግዥው ከ200,000.00 ብር በላይ የሚሆን ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
  9. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ ((ሲ.ፒ.ኦ.) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918 77 86 80 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።

ዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበር

ባሕር ዳር

Save Tender