የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት አቶ ካሳሁን ምስጋናው እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ደስታ ኪዳኔ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በ/ቁጥር 268999 በ12/9/2013 ዓ.ም በ22/2/2013 ዓ.ም እና በመ/ቁ 198 19/06/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአዲስ ከተማ ከ/ከተማ ወረዳ 7 የቤ.ቁ 74 የሆነው ድርጅት የገቢዎች ዓመታዊ ገቢ ግብር እዳ ብር 6,477,974.45 ያለበት የሚሸጠው ድርጅት የሚገዛው አካል በቤቱ ውስጥ የመሥራት መብት እንደሚገዛና ቤቱ ግን የመንግሥት ንብረት ሆኖ የሚቀጥልና ገዥው ግን የመንግሥት ንብረት ሆኖ ኪራይ ቤቶች (ካፌ ) የመንግሥት ቤቶች በፕሮፖርሽን ጋር የኪራይ ውል ፈጽሞ እንደሚከራይ ታውቆ ኪራይ ይፈፀማል የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 52,200.00 (ሀምሳ ሁለት ሺ ሁለት መቶ ብር) ሆኖ የትራንዛሽን ታክስ ዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሀሴ 25 ቀን 2014 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 05፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፈደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚርጧቸው ሶስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታhስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት
