Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 Sep 2022, 9:53 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍባለመብት አቶ በቀለ ተስፋዬ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ሮ ቅዱሳን ብርሃን መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 294320 በ28/1/2013 ዓ.ም እና በመ/ቁ 292160 በ23/10/2013 ዒ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ /ከተማ ወረዳ 03 የቤ.ቁ 223 በከሳሾችና ተካሰሾች ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት 267 ካ/ሜ መለያ ቁጥር AA00003030327 የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 538,320 (አምስት መቶ ሰላሳ ስምንት ሺ ሶስት መቶ ሃያ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ
ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል።የተጫራቾች ምዝገባ በ4:30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን
በባንክ በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል። 1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም።በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታከስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት

 

Save Tender